1ሙሴን እንዲህ አለው
2“ለእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ቅዱስ እንደሆንኩ እናተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡
3እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፣ እናንተም ሰንበቴን ጠብቁ፡፡ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡
4ጥቅም ወደሌላቸው ጣኦታት ዘወር አትበሉ፣ ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልዕክትን አታብጁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
5ለያህዌ የህብረት መስዋእቶችን ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ልታገኙ በምትችሉበት መንገድ አቅርቡ፡፡
6መስዋዕቱ ባቀረባችሁበት ቀን አሊያም በማግስቱ ይበላ፡፡ አንዳች ነገር እስ ሶተኛው ቀን ቢተርፍመ ይቃጠል፡፡
7በሶስተኛው ቀን ቢበላ የረከሰ ነው፡፡ ተቀባይነት አያገኝም፣
8ነገር ግን የበላው ሁሉ በበደለኛነቱ ይጠየቅበታል ምክንያቱም ለያህዌ የተለየውን አርክሷል፡፡ ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
9የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ፤ የእርሻችሁን ቀርጢያ ሁሉ አትልቀሙ፣ አሊያም የአዝመራችን ምርት ሁሉ አትሰብስቡ፡፡
10ከወይን ተክልህ እያንዳንዱን ወይን ፍሬ አትሰብስብ፣ አሊያም በወይን ስፍራ የወዳደቁትን የወይን ፍሬዎች አትልቀም፡፡ ለድሆችና ለመጻተኞች እነዚህን ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
11አትስረቁ፡፡ አትዋሹ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ፡፡
12በሃሰት በስሜ አትማሉ የአምላካችን ስም አታርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
13ጎረቤትህን አትበድል ወይም አትዝረፈው፡፡ የቀን ሰራተኛውን ክፍያ በአንተ ዘንድ አታሳድር፡፡
14መስማት የተሳነውን ሰው አትርገመው ወይም ከእውሩ ፊት ማሰናከያ ድንጋይ አታስቀምጥ ይልቁንም አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
15ፍትህን አታጣም፡፡ አንድ ሰው ድሃ ስለሆነ ልታደላለት አይገባም፣ እንደዚሁም አንድ ሰው ባለጸጋ ስለሆነ አታዳላለት፡፡ ይልቁንም ለጎረቤትህ በጽድቅ ፍረድ 16በሰዎች መሃል በሀሳት ሃሜትን አታሰራጭ
16በሰዎች መሃል ሀሜትን እያሰራጨህ አትዙር፣ ይልቁንም የጎረቤትህን ሕይወት አቅና፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
17በልብህ ወንድምህን አትጥላ፡፡ በእርሱ ምክንያት የኃጢአቱ ተካፋይ እንዳትሆን ጎረቤትህን በቅንነት ገስጸው፡፡
18ከህዝብህ ማንንም አትቀበል ወይም በማንም ላይ ቂም አይኑርህ፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
19ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለብህ፡፡ እንስሳትህን ከሌሎች ልዩ ዝርያ ካላቸው እንስሳት ጋር አታዳቅል፡፡ በእርሻህ ላይ ስትዘራ የተለያየ የዘር ዐይነቶችን አትደባልቅ፡፡ ከሁለት የተለያዩ አይነት ነገሮች ተደባልቆ የተሰራ ልብስ አትልበስ፡፡
20ቤዛ ካልተከፈለላት ወይም ነጻ ካልወጣች ለባል ከታጨት ባሪያ ከሆነች ልጃገረድ የተኛ ሁሉ ይቀጡ፡፡ ሊገደሉ ግን አይገባም ምክንያቱም ነጻ አልወጣችም፡፡
21ሰውዬው ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለበደል መስዋዕት ለያህዌ አውራ በግ ያምጣ፡፡
22ከዚያ ካህኑ በያህዌ ፊት ሰውዬው ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕት አውራ በግ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፡፡ ከዚያ የሠራው ኃጢአት ይቅር ይባልለታል፡፡
23ወደምድሪቱ ስትገቡና ለምግብ የሚሆን ሁሉንም ዐይነት ዛፎች ስትተክሉ፣ ዛፎቹ ያፈሩትን ፍሬ ለመብላት እንደተከለከለ ቁጠሩት፡፡ ፍሬው ለእናንተ ለሶስት ዓመታት የተከለከለ ነው፡፡ አይበላም፡፡
24ነገር ግን በአራተኛው አመት ፍሬው ሁሉ ለያህዌ ለምስጋና የሚሰዋ ቅዱስ ይሆናል፡፡
25አመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፡፡ በመጠበቃችሁ ዛፎቹ ብዙ ያፈራሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
26ደሙ በውስጡ ያለበትን ስጋ አትብሉ፡፡ ስለ ወደፊቱ መናፍስትን አታማክሩ፣ ደግም ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ኃይላት ሌሎችን ለመቆጣጠር አትፈልጉ፤፡፡
27እንደ ጣኦት አምላኪዎች የጸጉራችሁን ዙሪያ አትላጩ ወይም የጺማችሁን ዙሪያ አትቆረጡ፡፡
28ለሙታን ሰውነታችሁን በስለት አትቁረጡ ወይም በሰውነታችሁ ላይ ንቅሳት አታድርጉ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
29ሴት ልጅህን ሴተኛ አዳሪ በማድረግ አታወርዳት፣ በዚህ ነገር አገረ ወደ ግልሙትና ትገባለች ምድሪቱም በእርኩሰት ትሞላለች፡፡
30ጠብቁ የቤተመቅደሴን ቅድስና አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
31ወደ ሙታን ጠሪዎችና መናፍስትን ወደሚያነጋግሩ ዘወር አትበሉ፡፡ እነዚህን አትፈልጉ፣ ካልሆነ ያረክሷችኋል፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
32ፀጉሩ ለሸበተ ሰው ተነስለት ደግሞም በዕድሜ የገፋውን ሰው አክብር፡፡ አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
33በምድርህ በመካከልህ መጻተኛ ቢኖር፣ አትግፋው፡፡
34በመካከላችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ተወላጅ እስራኤላዊ ወገናችሁ ቁጠሩት ደግሞም እንደ ራሳችሁ ውደዱት፣ ምክንያቱም እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ነበራችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
35ርዝመትን፣ ክብደትን፣ ወይም ብዛትን ስትለኩ፡፡ ሀሰተኛ መለኪያ አትጠቀሙ፡፡
36ትክክለኛ መስፈሪያን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን፣ ትክክለኛ የኢፍ እና የኢን መለኪያዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
37ትዕዛዛቴንና ህግጋቴን ሁሉ ጠብቁ፣ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”