መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ከመገናኛው ድንኳን ሆኖ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፣
2“ለእስራኤላዊያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ከእናንተ መሃል ማንም ሰው ለያህዌ መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ከከብቶቻችሁ ወይም ከመንጋው እንስሳት መሃል አንዱን ያቅርብ፡፡
3መባው ከመንጋው መሃል የሚቃጠል መስዋዕት ከሆነ፣ ነውር የሌለበት ወንድ መስዋዕት ያቅርብ፡፡ መስዋዕቱ በያህዌ ፊት ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያቅርበው፡፡
4በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ እጁን ይጭናል፣ ይህም በእርሱ ምነትክ ያስተሰርይለት ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል፡፡
5ከዚያ በያህዌ ፊት ወይፈኑን ይረድ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ካህናቱ የአሮን ልጆች ደሙን ያቀርቡና በመሰዊያው ላይ ይረጩታል፡፡
6ከዚያም ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ቆዳ መግፈፍና ብልቶችንም ማውጣት ይኖርበታል፡፡
7ከዚያም ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ ዕሳት ይለኩሱና እንጨት ይጨምሩበታል፡፡
8ካህናቱ የአሮን ልጆች የስጋውን ብልቶች፣ የከብቱን ጭንቅላትና ስቡን በመስዋዕቱ ምድጃ ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ በስርዓት ይደረድሩታል፡፡
9ነገር ግን ካህኑ የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ማጠብ ይኖርበታል፡፡ በመስዋዕቱ ላይ የሚገኘውን ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕት አብርጎ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለእኔ ጣፋጭ ሽታ ይሆናል፤ ይህም ለእኔ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡
10ለመስዋዕት የሚያቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት ከመንጋው ከሆነ፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች መሃል ነውር የሌለበት ተባዕት መስዋዕት ማቅረብ አለበት፡፡
11በያህዌ ፊት መስዋዕቱን ከመሰዊያው በስተቀኝ በኩል ይረደው፡፡ ካህናቱ የአሮን ልጆች የመስዋዕቱን ከብት ደም በመሰዊያው ዙሪያ ሁሉ ይርጩት፡፡
12ከዚያ ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ጭንቅላቱንና ስቡን እንዲሁም ብልቶቹን ይቆራርጥ፡፡ ከዚያም በመሰዊያው በሚገኘው የሚነድ እንጨት ላይ በስርዓት ይደርድረው፡፡
13ነገር ግን የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፡፡ ከዚያ ካህኑ መባውን በሙሉ ያቅርብና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህም የሚቃጠል መስዋዕት ነው፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፤ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡
14“ካህኑ ለያህዌ የሚያቀርበው የሚቃጠል የወፎች መስዋዕት ከሆነ፣አንድ ወፍ ወይም ዕርግብ ማቅረብ አለበት፡፡
15ካህኑ መስዋዕቱን ወደ መሰዊያው ያመጣና አንገቱን ይቆለምመዋል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ደሙም በመሰዊያው ጎን ተንጠፍጥፎ ይፈሳል፡፡
16የወፉን ማንቁርትና በውስጡ ያሉትን ያስወግድ፣ ከዚያም አመድ በሚደፉበት ከመሰዊያው በስተ ምስራቅ ይወርውረው፡፡
17ክንፎቹን ይዞ ይሰንጥቀው፣ ነገር ግን ለሁለት አይክፈለው፡፡ ከዚያ ካህኑ በዕሳቱ ላይ ባለው እንጨት መሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።