መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣
2‹ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብላችሁ ንገረቸው፣ ‹ማንም ሰው ከሰውነቱ የሚወጣ የሚመረቅዝ ፈሳሽ ሲኖርበት፣ ንጹኅ አይደለም፡፡
3ንጹኅ የማይሆነ ከሚመረቅዝ ፈሳሽ የተነሳ ነው፡፡ ከሰውነቱ የሚወጣ ፈሳሽ ቢቀጥል ወይም ቢቆም ንጹህ አይደለም፡፡
4የሚተኛበት አልጋ ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፣ የሚቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፡፡
5አልጋን የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ ሰውየውም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹኅ አይደለም፡፡
6የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበት ሰው በተቀመጠበት ማናቸውም ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
7የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበትን ሰው አካል የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
8እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ሰው ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ ያ ሰው ልብሱን ማጠብና እርሱም በውሃ መታጠብ አለበት፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
9ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ኮርቻ ንጹኅ አይደለም፡፡
10ከዚያ ሰው በታች ያለን ማንኛውንም ነገር የነካ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፣ እነዚያን ነገሮች የተሸከመ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
11እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ማንም ቢሆን አስቀድሞ እጆቹን በውሃ ሳያጠራ ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
12እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበትን ሰው የነካ ማናቸውም አይነት የሸክላ ዕቃ ይሰበር፣ የእንጨት የተሰራ ማጠራቀሚያ ሁሉ በውሃ ይንጻ፡፡
13ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ ለመንጻቱ ለእራሱ ሰባት ቀናትን ይቁጠር፤ ከዚያ ልብሶቹን ይጠብ ሰውነቱን በምንጭ ውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
14በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ኖሶች ይውሰድና ወደ መገናኛ ድንኳን ያህዌ ፊት ይቅረብ፣ በዚያ ወፎቹን ለካህኑ ይስጥ፡፡
15ካህኑ አንዱን ለሀጢአት መስዋዕት እና ሌላውን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርባቸው፣ እናም ካህኑ ለሰውዬው ስለ ፈሳሹ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡
16የማንንም ሰው የዘር ፈሳሽ ሳይታሰብ በድንገት ከእርሱ ቢወጣ፣ መላ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡
17ማናቸውም የዘር ፈሳሽ የነካ ልብስ ወይም ሌጦ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
18አንዲት ሴትና አንድ ወንድ አብረ ቢተኙና ወደ እርሷ የዘር ፈሳሽ ቢተላለፍ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደሉም፡፡
19አንዲት ሴት የወር አበባ ሲፈሳት፣ ያለመንጻቷ ለሰባት ቀናት ይቀጥላል፣ እርሷን የነካ ሁሉ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
20በወር አበባ ወቅት የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ንጹህ አይደለም፤ እንደዚሁም የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይደለም፡፡
21አልጋውን የነካ ማንኛም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ ያሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
22የተቀመጠችበትን ማናቸውንም ነገር የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ ያ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
23በአልጋም ይሁን በማንኛም ነገር ላይ ብትቀመጥ የተቀመጠችበትን ነገር የነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
24ከእርሷ ጋር የተኛ ንጹህ ያልሆነ ፈሳሽ ቢነካ፣ ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ንጹህ አይደለም፡፡
25አንዲት ሴት ከወር አበባ ቀናት በኋላ ለብዙ ቀናት ደም መፍሰሱን ቢቀጥል፣ ይህም ከወር አበባ ጊዜያት በኋላ ፈሳሽ ቢኖርባት፣ ንጹኅ ባልሆነችባቸው ፈሳሽ ባለባት ጊዜያት ሁሉ፣ በወር አበባ ወቅት ላይ እንዳለች ሁሉ እርኩስ ይሆናል ንጹህ አይደለችም፡፡
26ደሟ በሚፈስባቸው ጊዜያት የምትተኛበት አልጋ ሁሉ በወር አበባ ወቅት እንደምትተኛበት እርኩስ ይሆናል፣ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ልክ በወር አበባ ወቅት እንደሚሆነ ንጹህ አይደለም፡፡
27ደግሞም ከእነዚህ ነገሮች ማናቸንም የነካ ሁሉ ንጹህ አይደለም፤ ልብሶቹን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡
28ነገር ግን ከደም መፍሰሳ ብትነጻ፣ ለራስዋ ሰባት ቀናትን ትቆጥራለች፣ እናም ከዚያ በኋላ ንጹኅ ናት፡፡
29በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ትወሰድና ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለካህኑ ትስጥ፡፡
30ካህኑ አንዱን ወፍ ለሀጢአት መስዋእት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፣ ስለ ፈሳሽም እርኩሰት በያህዌ ፊት ያስተሰርይላታል፡፡
31የእስራኤል ሰዎች ከእርኩሰታቸው የምትይች እንደዚህ ነ፣ ይህ ከሆነ በመካከላቸ የምኖርበትን ቤተ መቅደሴን በማርከስ በእርኩሰታቸ አይሞቱም፡፡
32ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚጣ፣ የዘረ ፈሳሹ ከእርሱ ለሚጣና ለሚያረክሰ ማንኛም ሰ ህግጋቱ እነዚህ ናቸ፡፡
33ለማንኛም በር አበባ ላይ ላለች ሴት፣ ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚፈሰ ሰ ሁሉ፣ ንድም ይሁን ሴት፣ እንዲሁም ንጹህ ካልሆነች ሴት ጋር ለሚተኛ ንድ ህጉ ይህ ነ፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።