መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“የታመመ ሰው በሚነጻበት ቀን ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡
3ካህኑ የሰውየው ተላላፊ የቆዳ በሽታ መዳኑን ለመመርመር ከሰፈር ይወጣል፡፡
4ከዚያም ካህኑ የሚነጻው ሰው ህይወት ያላቸው ሁለት ንጹህ ወፎችን፣ የጥድ ዕንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድርና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል፡፡
5ካህኑ የታመመው ሰው ከወፎቹ አንዱን አርዶ በሸክላ ማሰሮ ውስጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
6ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ፣የጥዱን እንጨትና፣ ደማቁን ቀይ ድርና ሂሶጵ ይቀበለውና ህይወት ያለውን ወፍ ጨምሮ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ቀደም ሲል በታረደው ወፍ ደምና ንጹህ ውሃ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡
7ከዚያ ካህኑ ይህንን ውሃ ከበሽታው በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፣ ከዚያ በኋላ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡
8የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፣ ፀጉሩን በሙሉ ይላጫል፣ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር ይመለስ፣ ነገር ግን ከድንኳኑ ውጭ ለሰባት ቀናት ይቆያል፡፡
9በሰባተኛው ቀን የራሱን ፀጉር በሙሉ ይላጭ፣ ልብሶቹን ይጠብ፣ ገላውን በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡
10በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸው ሁለት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣አንድ ነውር የሌለበት የአንድ አመት የበግ ጠቦት ያምጣ፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ የላመ ዱቄት እና አንድ ሊትር ዘይት ለእህል ቁርባን ያቅርብ፡፡
11የመንጻት ስርዓቱን የሚያስፈጽመው ካህን የሚነጻውን ሰው ከእነዚህ ነገሮች ጋር ይዞ፣ በያህዌ ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይቆማል፡፡
12ካህኑ ወንዱን ጠቦት ወስዶ ለኃጢአት መስዋዕት ከአንዱ ሊትር ዘይት ጋር ያቀርባል፤ እነዚህንም በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ይወዘውዘዋል፤ ለእርሱም ያቀርበዋል፡፡
13ወንዱን ጠቦት የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ባቀረቡበት ስፍራ በቤተ መቅደስ ያርደዋል፤ እንደ በደል መስዋዕቱ ሁሉ የኃጢአት መስዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፣ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
14ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባ፡፡
15ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ወስዶ በእርሱ በራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣
16ከዚያም በግራ እጁ መዳፍ ላይ በፈሰሰው ዘይት ውስጥ የቀኝ እጁን ጣት ያጠልቃል፣ በጣቱ ላይ ካለው ዘይት በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡
17ካህኑ በእጁ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት፣ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡ ይህንን ዘይት በበደል መስዋዕቱ ደም ላይ ያድርገው፡፡
18ካህኑ በእጁ የቀረውን ዘይት፣ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስስ፣ እናም ካህኑ በያህዌ ፊት የሚነጻውን ሰው ያሰርይለታል፡፡
19ከዚያ ካህኑ የኃጢአት መስዋዕቱን ይሰዋል፤ ደግሞም ንጹህ ባለመሆኑ ምክንያት መንጻት ላለበት ሰው ያሰርይለታል፣ እናም ከዚህ በኋላ የሚቃጠል መስዋዕቱን ይሰዋል፡፡
20ካህኑ የሚቃጠለውን መስዋዕትና የእህል ቁርባኑን በመሰዊያ ላይ ያቀርባል፡፡ ካሁኑ ለሰውየው ማስተስረያ ያቀርብለታል፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
21ሆኖም ሰውየው ደሃ ከሆነና እነዚህን መስዋዕቶች ማቅረብ ካልቻለ ለኃጢአቱ ማስተስረያ የበደል መስዋዕት አንድ ወንድ ጠቦት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄትና አንድ ሊትር ዘይት ያቅርብ፣
22ሰውየው በአቅሙ ከሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ጋር፣ አንደኛውን ወፍ የኃጢአት መስዋዕት ሌላኛው ደግሞ የሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡
23በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ወደ መገናኛው ድንኳን በያህዌ ፊት ያምጣቸው፡፡
24ከዚያ ካህኑ ጠቦቱን ለበደል መስዋዕት ደግሞም አንዱን ሊትር ዘይት፣ይወስድና ለያህዌ የበደል መስዋዕት ይወዘውዛል፣ እናም ለእርሱ እነዚህን ያቀርባቸዋል፡፡
25ለበደል መስዋዕት ጠቦቱን ያርዳል፣ እናም ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡
26ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ጥቂቱን በገዛ ራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣
27በቀኝ ጣቱ ከዘይቱ በግራ እጁ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡
28ከዚያ ካህኑ በእጁ ካለው ዘይት ጥቂቱን በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ የበደል መስዋዕቱን ደም ባደረገበት ተመሳሳይ ስፍራዎች ይቀባል፡፡
29የተረፈውን በእጁ ያለውን ዘይት ያስተሰርይለት ዘንድ በያህዌ ፊት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሳል፡፡
30ሰውየው በአቅሙ ካቀረበው ከእርግቦቹ ወይም ከዋኖሶቹ አንዱን ይሰዋ -
31ከእህል ቁርባኑ ጋር፣ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ከዚያም ካህኑ ለሚነጻው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡
32ለመንጻት ዋናውን መስዋዕት ማቅረብ ለማይችል ተላላፊ የቆዳ በሽታ ላለበት ሰው የመንጻት ህጉ ይህ ነው፡፡”
33ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣
34“ርስት አድርጌ ወደሰጠኋችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትመጡ፣ ርስት በሆናችሁ ምድር በቤታችሁ እየሰፋ የሚሄድ ብክለት ባደርግባችሁ፣
35የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ይናገር፡፡ እንዲህም ይበል፣ “በቤቴ ብክለት ያለ ይመስለኛል፡፡’
36ከዚያ ካህኑ በቤቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ነገር እርኩስ እንዳይሆን ብክለት መኖሩን ለማየት ወደዚያ ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉ ያዛል፣ ከዚህ አስቀድሞ ካህኑ ያንን ቤት ለማየት ይገባል፡፡
37ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መኖሩን፣ ደግሞም አረንጓዴ ሆኖ ወይም ቀላ ብሎ በግርግዳዎቹ ላይ መታየቱን ይመርምር፡፡
38ቤቱ ሻጋታ ካለው፣ ካህኑ ከዚያ ቤት ይወጣና ለሰባት ቀናት በሩን ይዘጋዋል፡፡
39በሰባተኛው ቀን ካህኑ ተመልሶ ይመጣና ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መስፋፋቱን ለማየት ይመረምራል፡፡
40እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ሻጋታ የተገኘባቸውን ድንጋዮች ከግድግዳው ላይ እየፈነቀሉ እንዲያወጡና ከከተማ ውጭ ቆሻሻ ስፍራ መጣያ እንዲጥሏቸው ያዛል፡፡
41የቤቱ የውስጥ ግድግዳዎች ሁሉ እንደዲፋቁ ይጠይቃል፣ እነርሱም እየተፋቁ የተነሱትን የተበከሉትን ቁሶች ከከተማ አውጥተው በቆሻሻ መጣያ ስፍራ ይጥላሉ፡፡
42ባስወገዷቸው ድንጋዮች ስፍራ ሌሎች ድንጋዮች ወስደው ያስቀምጡ፣ ቤቱን ለመምረግ አዲስ ጭቃ ይጠቀሙ፡፡
43ድንጋዮቹ ተነስተውና ግርግዳው ተፍቆ እንዲሁም ተለስኖ ዳግም ብክለቱ ከወጣና ከታየ፣
44ካህኑ ብክለቱ መስፋፋቱን ለመመልከት ቤቱን ይመርምር፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ይህ ጎጂ ብክለት ነው፤ ቤቱ ንጹህ አይደለም፡፡
45ቤቱ ይፍረስ፡፡ የቤቱ ድንጋዮች፣ በሮች፣ እና ፍርስራሾች ከከተማ ውስጥ በቆሻሻ መጣያ ይጣል፡፡
46በተጨማሪም፣ ቤቱ በተዘጋባቸው ጊዜያት ወደዚያ ቤት የሄደ ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡
47ማንም በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እንዲሁም በዚህ ቤት ውስጥ የተመገበ ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡
48ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ ወዴት እንደተስፋፋ ለመመርመር ካህኑ ወደዚያ ቤት ቢገባ፣ እናም ብክለቱ ተወግዶ ቢሆን ቤቱ ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
49ከዚያ ካህኑ ቤቱን ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የጥድ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድር እና ሂሶጵ ይውሰድ፡፡
50ከወፎቹ አንዱ ንጹህ ውሃ በያዘ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርደዋል፡፡
51የጥድ እንጨት፣ሂሶጵደማቅ ቀይ ድር እና በህይወት ያለ ወፍ ይውድና በታረደው ወፍ ደም ውስጥ እና በንጹህ ውሃ ውስት ይነክራቸዋል፣ከዚያም ቤቱን ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡
52ቤቱን በወፉ ደምና በንጹህ ውሃ፣ በህይወት በሚገኘው ወፍ፣ በጥድ እንጨት፣በሂሶጵና በደማቅ ቀይ ድር ያነጻዋል፡፡
53በህይወት የሚገኘውን ወፍ ግን ከከተማ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡ በዚህ መንገድ ቤቱን ያስተሰርያል፣ ቤቱም ንጹህ ይሆናል፡፡
54ለሁሉም አይነት ተላላፊ የቆዳ በሽታና እንዲህ ያለውን በሽታ ለሚያመጡ ነገሮች፣ እንዲሁም ለሚያሳክክ ህመም፣
55እንዲሁም ለልብስና ለቤት ብክለት፣
56ለእብጠት፣ ለሚያሳክክ ህመም፣ እና ለቋቁቻ፣
57በእነዚህ ሁኔታዎች እርኩስና ንጹህ የሚሆነውን ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።