መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 16

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረ፡ - ይህ የሆነ የአሮን ሁለቱ ልጆች ¨ደ ያህ«ከቀረቡና ከሞቱ በሀላ ነበር፡፡
2ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለ፣ “ለ¨ንድምህ ለአሮን እንዲህ ብለህ ተናገረ፣ በፈለገ¬ ጊዜ ሁሉ በመጋረጃ ¬ስጠኛ ¨ዳለ ¨ደ ቅድስተ ቅዱሳኑ፣ በታቦቱ ላይ ወዳለ ወደ ማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ላይ እገለጣለሁ፡፡
3ስለዚህም አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መቅረብ ያለበት እንደዚህ ነው፡፡ ለሀጢአት መስዋዕት ወይፈን፣ ለሚቃጠል መስዋዕት አ¬ራ በግ ይዞ መግባት አለበት፡፡
4ቅዱሱን በፍታ ቀሚስ ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ የስጥ ሱሪ ይልበስ፣ ደግሞም የበፍታ መጠምጠሚያ የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፡፡ ቅዱሳኑ አልባሳት እነዚህ ናቸው፡፡ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብና እነዚህን ልብሶች ይልበስ፡፡
5ከእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁለት ወንድ ፍየሎችን ለሀጢአት መስዋዕት እንዲሁም አንድ አ¬ራ በግ ለሚቃጠል መስዋዕት ይውሰድ፡፡
6ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማ¬ን ለኃጢአት መስዋዕት ያቅርብ፣ ይህም ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ነው፡፡
7ቀጥሎም ሁለቱም ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ¬ ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ ፊት ያቁማቸው፡፡
8ከዚያ አሮን በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል፣ አንዱን ዕጣ ለያህዌ ሌላ¬ን ዕጣ ለሚለቀቀው ፍየል ይጣል፡፡
9ከዚያም አሮን ዕጣ ለያህ«የ¨ጣለትን ፍየል ያቀርባል፣ ያንን ፍየልም ለኃጢአት መስªዕት ያቀርበªል፡፡
10ለመለቀቅ ዕጣ የጣትን ፍየል ግን ወደ ምድረበዳ በመልቀቅ ለስርየት ከነህይ¨ት ለያህዌ መቅረብ አለበት፡፡
11ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማን ለሀጢአት መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ማድረግ አለበት፣ ስለዚህ ኮርማን ለራሱ የሀጢአት መስዋዕት አድርጎ ይረዳ፡፡
12አሮን በያህዌ ፊት ከመሰዊያ የከሰል እሳት የሞላውን ማጠንት ይውሰድ፣ በእጆቹ ሙሉ የላመ ጣፋጭ ዕጣን ይያዝና እዚህንም ነገሮች ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡
13በዚያም በያህ«ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምር፣ ከእጣኑ የሚ¨ጣ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለ የማስተሰርያን ክዳን ይሸፍናል፡፡ እንዳይሞት ይህንን ያድርግ፡፡
14ከዚያም ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውሰድና በጣቱ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ ከደሙ ጥቂት ¨ስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡
15ከዚያም ለህዝቡ ኃጢአት የኃጢአት መስªዕት ፍየሉን ይረድና ደሙን ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ በዚያም በኮርማ ደም እንዳደረገ ሁሉ ያድርግ በማስተሰርያ¬ ክዳን ላይ ደሙን ይርጭ ከዚያም በማስተሰርያ¬ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡
16በእስራኤል ህዝብ ያልተቀደሱ ተግባራት፣ በአመጻቸ¬ና በኃጢአቶቻቸ¬ ሁሉ ምክንያት ለተቀደሰ ስፍራ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡ ንጹህ ያልሆኑ ተግባሮቻቸ¬ በታዩ ጊዜያት፣ ያህ በመካከላቸ¬ ለሚያድርበት ለመገናኛ¬ ድንኳንም ይህን ያድርግ፡፡
17አሮን ለማስተሰርይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚገባበት ሰዓትና እንዲሁም ለእርሱ፣ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ማስተሰርዩን እስከሚጨርስ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝም፡፡
18በያህ«ፊት ወዳለ መሰዊያ ይሂድና መሰዊያን ያስተሰርይ፣ ከኮርማ ደም ጥቂት እንዲሁም ከፍየሉ ደም ጥቂት ይ¬ስድና በመሰዊያ ዙሪያ ባሉ ቀንዶች ሁሉ ¬ስጥ ያስነካ፡፡
19መሰዊያዉን ንጹህ ካልሆነ የእስራኤል ሰዎች ድርጊቶች ለማንጻትና ለያህዌ ለመለየት በላዩ ካለ ጥቂት ደም ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ፡፡
20ቅድስተ ቅዱሳኑን፣ የመገናኛን ድንኳንና መሰዊያን ማስተሰርያ¬ን ሲጨርስ በህይወት የሚገኘ¬ን ፍየል ያቅርብ፡፡
21አሮን ህይወት ባለው ፍየል ላይ ሁለቱንም እጆቹን ይጫንና የእስራኤልን ህዝብ በደልን ሁሉ፣ አመጻቸውን ሁሉ፣ እና ሀጢአታቸውን ሁሉ በላዩ ላይ ይናዘዝበት፡፡ ከዚያም ያንን ሃጢአተኛነት በፍየሉ ራስ ላይ አድርጎ ፍየሉን ወደ በረሃ ለመስደድ ኃላፊነት ባለበት ሰው አማካይነት ወደ በረሃ ያባው፡፡
22ፍየሉ የሰ­ቹን በደል ሁሉ ይሸከምና ገለልተኛ ¨ደ ሆነ ስፍራ ይሄዳል፡፡ በበረሃ ስፍራም፣ ሰ¬ዬ¬ ፍየሉን ይለቀªል፡፡
23ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳን ይመለስና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመሄዱ አስቀድሞ የለበሰን የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፣ እነዚያን ልብሶችም በዚያ ስፍራ ያስቀምጣቸዋል፡፡
24በተቀደሰ ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያም የዘወትር ልብሱን ይልበስ፣ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መስዋዕቱን የህዝቡን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መንገድ ለራሱና ለህዝቡ ማስተሰርያ ያቀርባል፡፡
25በመሰዊያ ላይ የኃጢአት መስዋዕቱን ስብ ያቃጥል፡፡
26የሚሰደደውን ፍየል የለቀቀው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
27በተቀደሰው ስፍራ ለማስተሰርያው ደማቸው የቀረበው የኃጢአት መስªዕቱ ኮርማ እና የኃጢአት መስªዕቱ ፍየል ከሰፈር ውጭ ይውስዳቸው። በዚያም ቆዳቸውን፣ ስጋቸውንና ፈርሳቸውን ያቃጥላFቸው፡፡
28እነዚህን የእንስሳውን ክፍሎች የሚያቃጥለው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ፣ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
29በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በአስረኛው ቀን ራሳችሁን ትሁት ታደርጋላችሁ ስራም አትሰሩበትም ለእናንተም ሆነ ለመጻተኛው ይህ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፡፡
30ይህ የሚሆነው በዚህ ዕለት በያህዌ ፊት ቅዱስ ትሆኑ ዘንድ ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ እንድትነጹ ማስተሰርያ ስለሚደረግላችሁ ነው፡፡
31ይህ ለእናንተ ክቡር ሰንበት ዕረፍት ነው፣ ራሳችሁን ትሁት ማድረግ አለባችሁ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡ይህ በእናንተ መሀል ሁልጊዜም መታሰቢያ ነው
32ሊቀ ካህኑ፣ በአባቱ ስፍራ ሊቀካህን ሊሆን የሚቀባውና የሚሾመው፣ ይህን ማስተሰርያ ማስፈጸምና ቅዱስ የሆነውን የበፍታ ልብሶች መልበስ አለበት፡፡
33ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመስዋዕቱ፣ ማስተሰርያ ያደርጋል፤ እንደዚሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሰዎች በሙሉ ማስተሰርያ ያደርጋል፡፡
34"ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፣ ለእስራኤል ሰዎች ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ማስተሰርያ ለማቅረብ ይህ በየአመት አንድ ጊዜ ይደረግ፡፡” ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተደረገ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።