መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
2“ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ችፍታ ወይም ቋቁቻ ቢወጣና ቢቆስል በሰውነቱ ላይ የቆዳ በሽታ ይሆናል፣ በዚህ ጊዜ ወደ ሊቀካህኑ አሮን ይምጣ፣ አሊያም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ይምጣ፡፡
3ከዚያ በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን በሽታ ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ በበሽታው ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ፣ እና በሽታው በቆዳው ላይ ከሚታየው ይልቅ የከፋ ሆኖ ከተገኘ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ካህኑ ከመረመረው በኋላ፣ ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡
4በቆዳው ላይ የታየው ቋቁቻ ነጭ ከሆነ፣ እና ወደ ቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ እንዲሁም በህመሙ አካባቢ የሚገኘው ጸጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ፣ ካህኑ በሽታው ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያገልግለው፡፡
5በሰባተኛው ቀን፣ ካህኑ በእርሱ እይታ በሽታው አየከፋ በቆዳው ላይ እየሰፋ አለመሄዱን ለማየት ይመርምረው፡፡ በሽታው ለውጥ ካላሳየ፣ ካህኑ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ሰውየውን አግልሎ ያቆየው፡፡
6በሰባተኛው ቀን በሽታው እየተሻለው እንደሆነና በቆዳው ላይ እየሰፋ እንደላሆነ ለማየት ካህኑ ሰውየውን ደግሞ ይመረምረዋል፡፡ በሽታው ለውጥ ካለው፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆነኑን ይገልጻል፡፡ ይህ ሽፍታ ነው፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚህ በኋላ ንጹህ ነው፡፡
7ነገር ግን ሰውየው ራሱን ለካህን ካሳየ በኋላ ሽፍታው በቆዳው ላይ ከተስፋፋ፣ እንደገና ራሱን ለካህን ያሳይ፡፡
8ሽፍታው ይበልጥ በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ መሆኑን ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ከተስፋፋ፣ ከዚያ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አይደለም ይላል፡፡ ይህ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ነው፡፡
9ተላላፊ የቆዳ በሽታ በአንድ ሰው ላይ ሲገኝ፣ ይህ ሰው ወደ ካህን ይምጣ፡፡
10ካህኑ በሰውየው ቆዳ ላይ ነጭ ዕብጠት መኖሩን ለማየት ይመረምረዋል፣ ጸጉሩ ወደ ነጭነት መቀየሩን፣ ወይም በዕብጠቱ ላይ የስጋ መላጥ መኖሩን ይመልከት፡፡
11እንዲህ ያለ ነገር ካለ፣ ይህ ጽኑ የቆዳ ህመም ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፡፡ ሰውየውን አያገለውም፣ ምክንያቱም ቀድሞውኑም ንጹህ አይደለም፡፡
12በሽታው በቆዳው ላይ በሰፊው ጎልቶ ከታየና የሰውየውን ቆዳ ከአናቱ እስከ እግሩ ከሸፈና፣ ካህኑ ይህ እስከ ታየው ድረስ፣ በሽታው የሰውየውን አካል ሸፍኖት እንደሆነ ለማየት ይመርምረው፡፡
13እንዲህ ሆኖ ከተገኘ፣ በሽታው ያለበት ሰው ንጹህ አለመሆኑን ካህኑ ይግለጽ፡፡ ሁሉም ወደ ንጣት ተለውጦ ከሆነ ንጹህ ነው፡፡
14ነገር ግን የስጋ መላጥ ከታየበት፣ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡
15ካህኑ የስጋውን መላጥ ማየትና ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፣ ምክንያቱም የተላጠ ስጋ ንጹህ አይደለም፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
16ነገር ግን የተላጠው ስጋ መለልሶ ነጭ ቢሆን፣ ሰውየው ወደ ካህኑ ይሂድ፡፡
17ካህኑ ስጋው ወደ ነጭነት ተመልሶ እንደሆነ ይመረምረዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ይገልጻል፡፡
18አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ወጥቶ ሲድን፣
19እና በዕባጩ ስፍራ እብጠት ወይም ቋቁቻ፣ ቀላ ያለ ንጣት፣ ሲኖር ይህን ካህኑ ሊያየው ይገባል፡፡
20ካህኑ ይህ ወደ ታማሚው ቆዳ ዘልቆ የገባ መሆኑን እና በዚያ ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት መለወጡን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቃል፡፡ እብጠቱ በነበረበት ስፍራ እየሰፋ ከሄደ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
21ነገር ግን ካህኑ ይህንን መርምሮ በውስጡ ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ከተመለከተ፣ እና ይህም ከቆዳው ስር ካልሆነ ሆኖም ከደበዘዘ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
22በቆዳው ላይ በሰፊው ከተስፋፋ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አይደለም ይበል፡፡ ይህ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
23ነገር ግን ቋቁቻው በቦታው ከሆነና ካልተስፋፋ፣ ይህ የእባጩ ጠባሳ ነው፣ እናም ካህኑ ንጹህ ነው ብሎ ያስታውቅ፡፡
24አንድ ሰው ቆዳው ቃጠሎ ሲኖርበትና የስጋው መላጥ ቀላ ያለ ንጣት ወይም ነጭ ጠባሳ ሲሆን፣
25ካህኑ ያጠባሳ ስፍራ ወደ ንጣት መለወጡን እና ወደ ቆዳው ዘልቆ መግባቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንደዚህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ከቃጠሎው አልፎ ከውስጥ የመጣ ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
26ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ በስፍራው ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ቢደርስበትና ቁስሉ ከቆዳው ስር ሳይሆን ቢቀር እየከሰመ ቢመጣ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
27ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ይመርምረው፡፡ ምልክቱ በሰፊው በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፣ ካህኑ ንጹህ አይደለም ብሎ ያሳውቅ፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
28ምልክቱ በስፍራው ከቆየና በቆዳው ላይ እየሰፋ ካልሄደ ነገር ግን ከከሰመ ይህ በቃጠሎው የመጣ እብጠት ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፣ ይህ ከቃጠሎው የመጣ ጠባሳ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡
29በአንድ ወንድ ወይም ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ተላላፊ በሽታ ቢኖር፣
30ችግሩ ከቆዳው ስር የዘለቀ መሆኑና በላዩ ቢጫ ስስ ጸጉር እንዳለ ለማየት ካህኑ ካህኑ የተላላፊ በሽታ ምርመራ ያድርግለት፡፡ ይህ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ይህ የሚያሳክክ በሽታ ነው፣ በራስ ወይም አገጭ ላይ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
31የሚያሳክከውን በሽታ መርምሮ ከቆዳ ስር ያልዘለቀ መሆኑን ቢያይ፣ ደግሞም በውስጡ ጥቁር ጸጉር ባይኖር፣ ካህኑ ሰውየውን በሚያሳክክ በሽታው ምክንያት ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
32በሰባተኛው ቀን በሽታው ተስፋፍቶ እንደሆነ ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ቢጫ ጸጉር ከሌለና፣ በሽታው ላይ ላዩን ብቻ ከታየ፣
33ሰውየው ይላጭ፣ ነገር ግን በሽታው የሚገኝበት ዙሪያ መላጨት የለበትም፣ እናም ካህኑ የሚያሳክክ በሽታ ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
34በሰባተኛው ቀን በሽታው በቆዳው ላይ መስፋፋቱን ማቆሙን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያደርጋል፡፡ በሽታው ቆዳውን ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ ካህኑ የሰውየውን ንጹህ መሆን ያሳውቅ፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
35ነገር ግን ካህኑ ንጹህ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ ከሄደ ፣
36ካህኑ ዳግም ይመርምረው፡፡ በሽታው በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ ከሄደ፣ካህኑ ቢጫ ጸጉር መኖሩን መፈለግ አይኖርበትም፡፡ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡
37ነገር ግን ካህኑ ሰውየውን የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ መሄዱን እንዳቆመ ከተመለከተ ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፡፡
38አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ነጭ ምልክቶች ቢወጣ
39ምልክቱ ዳለቻ መልክ ያለው በቆዳ ላይ የወጣ ሽፍታ ብቻ መሆኑን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግ፡፡ ሰውየው ንጹህ ነው፡፡
40የሰውየው ጸጉር ከራሱ ላይ ካለቀ፣መላጣ ነው፣ ነገር ግን ንጹህ ነው፡፡
41ደግሞም ከፊት ለፊት ጸጉሩ ተመልጦ ራሰ በራ ቢሆንም ንጹህ ነው፡፡
42ነገር ግን በህመም ምክንያት ፈዘዝ ያለ ቅላት በተመለጠው ራሱ ላይ ወይም በግምባሩ ላይ ቢኖር፣ ይህ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የመጣ ነው፡፡
43በቆዳ ላይ ተላላፊ በሽታ ሲኖር እንደሚታየው በመላጣው ወይም በበራው ላይ በህመሙ ዙሪያ ፈዘዝ ያለ ቅላት መኖሩን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግለት፡፡
44ይህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ አለበት እናም ንጹህ አይደለም፡፡ በእርግጥ ካህኑ ሰውየው በራሱ ላይ ካለበት በሽታ የተነሳ ንጹህ እንደልሆነ ያስታውቅ፡፡
45ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፣ ጸጉሩን በከፊል ይሸፍን፣ እስከ አፍንጫው ይከናነብና ‘እርኩስ ነኝ፣ እርኩስ ነኝ’ እያለ ይጩህ፡፡
46ተላላፊው በሽታ ባለበት ቀናት ሁሉ እርኩስ ነው፡፡ እየሰፋ ሊሄድ በሚችል በሽታ ምክንያት ንጹህ ስላልሆነ፣ ለብቻው ይኑር፡፡ ከሰፈር ውጭ ይኑር፡፡
47በማናቸውም ነገር የተበከለ የሱፍም ሆነ የተልባ ዕግር ጨርቅ፣
48ወይም ከሱፍም ሆነ ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ፣ ወይም ቆዳም ሆነ ከቆዳ በተሰራ ልብስ -
49በልብሱ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ብክለት ቢገኝበት፤ በቆዳው፣ በተጠለፈው ወይም በተሰፋው ነገር፣ ወይም ማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ለይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ካህኑ ይህን ይመልከት፡፡
50ካህኑ የሚበከለውን ዕቃ ይመርምር፣ የተበከለውን ማናቸውንም ነገር ለሰባት ቀናት ይለየው፡፡
51በሰባተኛው ቀን እንደገና ብክለቱን ይመርምር፡፡ በልብሱ ወይም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ በተሸመነው ወይም በተጠለፈው ማናቸውም ልብስ ላይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ወይም በቆዳ ወይም ከቆዳ በተሰራ ማናቸውም ነገር ላይ ብክለቱ ቢሰፋ ጎጁ ነው፣ እናም ዕቃው ንጹህ አይደለም፡፡
52ካህኑ ያንን ልብስ ያቃጥል፣ ወይም ማናቸውም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ነገር፣ ማናቸውም ጎጂ ብክለት የተገኘበት ነገር በሽታ ያመጣልና ያቃጥለው፡፡ ዕቃው ሙሉ ለሙሉ ይቃጠል፡፡
53ካህኑ ዕቃውን መርምሮ ብክለቱ በልብ ወይም በተሸመነው ወይም በተለጠፈው ልብስ ወይም በቆዳ ዕቃዎቹ ላይ እየሰፋ የሚሄድ አለመሆኑን ካወቀ፣
54ብክለቱ የተገኘባቸውን ዕቃዎች እንዲያጥቡ ያዛቸዋል፤ ደግሞም ዕቃውን ለሰባት ቀናት ያግልል፡፡
55ከዚያ ካህኑ የተበከለውን ዕቃ ከታጠበ ከሰባት ቀናት በኋላ ይመረምረዋል፡፡ ብክለቱ ቀለሙን ካልቀየረውና እየሰፋ ባይሄድ እንኳን ንጹህ አይደለም፡፡ ብክለቱ የትም ላይ ይሁን ዕቃዎቹን አቃጥሏቸው፡፡
56ካህኑ ዕቃውን ከመረመረና ልብሱ ከታጠበ በኋላ ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ከተበከለው የልብሱ ወይም የቆዳው ክፍል ወይም ከተሸመነው ወይም ከተጠለፈው ዕቃ ቀድዶ ያውጣው፡፡
57እንዲህም ሆኖ ብክለቱ አሁንም በተሸመነው ወይም በተጠለፈው፣ ወይም በማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ላይ ከተገኘ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ብክለት ያለበትን ማናቸውንም ነገር አቃጥለው፡፡
58ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተሰራ ወይም የተለጠፈ ልብስ ወይም ማናቸውም ነገር፣ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ማናቸውም ነገር - ስታጥበው ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ዕቃው ዳግመኛ ይታጠብ እናም ንጹህ ይሆናል፡፡
59ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ለተሸመነ ወይም ለተጠለፈ፣ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ ለተሰራ ማናቸውም ነገር ብክለት ህጉ ይህ ነው፣ ስለዚህ ንጹህ ነው ወይም እርኩስ ነው ብለህ ማሳወቅ ትችላለህ፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።