1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“ለእስራኤል ሰዎች እንደህ በላቸው፣ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ወቅት ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለችም፡፡
3በስምንተኛው ቀን ህጻኑ ልጅ መገረዝ አለበት፡፡
4ከዚያ የእናቲቱ ከደሟ መንጻት ለሰላሳ ሶስት ቀናት ይቆያል፡፡ ምንም አይነት የተቀደሰ ነገር መንካት የለባትም ወይም የመንጻቷ ቀናት እስኪፈጸም ድረስ ወደ ቤተመቅደስ አትምጣ፡፡
5ሴት ልጅ ከወለደች፣ በወር አበባዋ ወቅት እንደነበረችው ለሁለት ሳምንታት ንጹህ አትሆንም፡፡ ከዚያ የእናትየው የመንጻት ስርዓት ለስድስት ቀናት ይቀጥላል፡፡
6ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ የመንጻቷ ቀናት ሲያበቃ ለካህኑ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ የአንድ አመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት ዋኖስ ወይም ዕርግብ ታቅርብ፡፡
7ከዚያ ካህኑ መስዋዕቱን በያህዌ ፊት ይሰዋና ያስተሰርይላታል፣ እናም ከደሟ መፍሰስ ንጹህ ትሆናለች፡፡ ወንድም ይሁን ሴት ልጅ ለወለደች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡
8ጠቦት ማቅረብ ባትችል፣ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት ርግቦች ትውሰድ፣ አንዱን ለሚቀጠል መስዋዕት ሌላውን ለኃጢአት መስዋዕት ታቅርብ እናም ካህኑ ያስተሰርይላታል፣ ከዚያም ንጹህ ትሆናለች፡፡’”