መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በሏቸው፣ ‘በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ የምትመገቧቸው ህያዋን ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡
3የተሰነጠቀ ሰኮና ያላቸውንና የሚያመሰኩትን ትመገባላችሁ፡፡
4ሆኖም፣ የሚያመሰኩ ቢሆኑም ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የሌላቸውን እንደ ግመል ያሉትን አትብሉ፤ምክንያቱም ያመሰኳሉ ነገር ግን ሰኮናው አልተሰነጠቀም፡፡ ስለዚህ ግመል ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
5እንዲሁም ሽኮኮ ያመሰኳል ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የለውም፣ ይህም ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
6ጥንቸል ቢያመሰኳም የተሰነጠቀ ሰኮና ስለሌለው ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
7አሳማ የተሰነጠቀ ሰኮና ቢኖረውም፣ አያመሰኳም ስለዚህ ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
8የእነዚህን ስጋ ፈጽሞ አትብሉ፣ ጥንባቸውንም አትንኩ፡፡ እነርሱ ለእናንተ ንጹህ አይደሉም፡፡
9በውቂያኖስም ሆነ በባህር በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት የምትበሏቸው ክንፍና ቅርፊት ያላቸው ናቸው፡፡
10ነገር ግን በውቂያኖስ ወይም በባህር የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ህያዋን ፍጥረታት ሁሉ፣በውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ጨምሮ እንዲሁም በውሃ ውስጥ ያሉት እንዲህ ያሉ ህያዋን ፍጥረታት በሙሉ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡
11ጸያፍ ሊሆኑ ስለሚገባቸውም፣ ስጋቸውን ልትበሉ አይገባም፣ እንደዚሁም በድናቸውም ጸያፍ ነው፡፡
12በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ቅርፊት የሌላቸው እንስሳት ሁሉ፣በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡
13ልትጸየፏቸው የሚገቡና የማትበሏቸው ወፎች እነዚህ ናቸው፤ ንስር፣ ጥንብ አንሳ፣
14ጭላት፣ ማንኛውም አይነት የሎስ
15ማንኛውም አይነት ቁራ፣
16የተለያ አይነት ጉጉት፣ የባህር ወፍ እና ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፡፡
17ትናንሽና ትላልቅ ጉጉቶችን ትጸየፋላችሁ፣ርኩምና ጋጋኖ፣
18የተለያዩ ጉጉቶች፣ ይብራ፣
19ሽመላ፣ ማናቸውም ዐይነት የውሃ ወፍ፣ ሳቢሳ፣ ጅንጁላቲ ወፍና የለሊት ወፍ፡፡
20በእግራቸው የሚራዱ ክንፍ ያላቸው በራሪ ነፍሳት በሙሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው፡፡
21ሆኖም ግን ከእግራቸው በላይ በምድር ላይ የሚፈናጠሩበት አንጓ ያላቸውን ማናቸውንም የሚበሩ ነፍሳት መብላት ትችላላችሁ፡፡
22እንደዚሁም ደግሞ ማናቸውንም ዐይነት አንበጣ፣ ትልቅ የአንበጣ ዝርያ፣ ፌንጣና ዝንቢት መብላት ትችላላችሁ፡፡
23ነገር ግን አራት እግር ያላቸው የሚበሩ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡
24ከእነዚህ እንስሳት ውስጥ የአንዱን በድን ብትነኩ እስከ ማታ ድረስ የረደሳችሁ ናችሁ፡፡
25ከእነዚህ የአንዱን በድን ያነሳ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ነው፡፡
26ማንኛውም ሙሉ ለሙሉ ያልተሰነጠቀ ሰኮና ያለው እንስሳ ወይም የማያመሰኳ እንስሳ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ነው፡፡ እነዚህን የነካ ሁሉ ይረክሳል፡፡
27በአራት እግሩ ከሚራመድ እንስሳ መሃል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሁሉ በእናንተ ዘንድ እርሱስ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን የነካ እስከ ማታ እርኩስ ነው፡፡
28እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን ያነሳ ልብሱን ይጠብ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ እነዚህ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ ናቸው፡፡
29በምድር ላይ ከሚሳቡ እንስሳት መሃል፣ በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡ አቁስጣ፣ አይጥ፣ ማናቸውም አይነት እንሽላሊት
30ትንሽ የቤት ላይ እንሽላሊት እና እስስት
31ከሚሳቡ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የሞቱትን አንዳቸውን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርሱስ ይሆናል፡፡
32ከእነዚህ መሃል አንዱ ሞቶ በማናቸውም ከእንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቆዳ ወይም ከበርኖስ በተሰራ ነገር ላይ ቢወድቀቅ ያዕቃ እርኩስ ይሆናል፡፡ ዕቃው ምንም ይሁን ለምንም አይነት ተግባር ይዋል ውሃ ውስጥ ይነከር እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
33ንጹህ ያልሆነ እንስሳ የገባበት ወይም የነካው የሸክላ ማሰሮ እንዲሁም በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ እርኩስ ይሆናል፤ ያንን ማሰሮ ሰባብረው፡፡
34ማናቸውም ለመበላት የተፈቀደ ምግብ፣ ንጹህ ካልሆነ ማሰሮ ውሃ ቢገባበት እርኩስ ይሆኖል፡፡ እንዲህ ካለው ማሰሮ ማንኛውም ነገር ቢጠጣ ያረክሳል፡፡
35እርኩስ ከሆነ እንስሳ በድን ማናቸውም አካሉ የወደቀበት ምድጃም ሆነ የማብሰያ ሸክላ እንዲሁም ማንኛውም ነገር ይረክሳል፡፡ ይሰባበር፡፡ እርኩስ ነው፣ በእናንተም ዘንድ የተጠላ ይሁን፡፡
36የመጠጥ ውሃ የሚገኝበት ምንጭ ወይም የውሃ ጉድጓድ እንዲህ ያሉ እንስሳት ቢገኙበትም ንጹህ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በውሃው ውስጥ የሚገኘውን እርኩስ የሆነውን በድን ቢነካ እርኩስ ይሆናል፡፡
37ንጹህ ያልሆነ እንስሳ በድን በዘር ላይ ቢወድቅ፣ እነዚያ ዘሮች የረከሱ ይሆናሉ፡፡
38ነገር ግን በዘሮቹ ላይ ውሃ ቢፈስ ንጹህ ያልሆነው እንስሳ በድን ማንኛውም አካል የተክል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ በእናንተ ዘንድ እርኩስ ይሆናል፡፡
39ለመበላት ከተፈቀደው እንስሳ አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የነካው ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡
40ደግሞም እንዲህ ያለውን በድን ያነሳ ሰው ልብሱን ያጥባል፣ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡
41ማንኛውም በምድር ላይ የሚሳብ እንስሳ ጸያፍ ነው፤ አይበላም፡፡
42በሆዱ የሚሳብ እንስሳ ሁሉ፣ እና በአራቱም እግሮቹ የሚራመድ፣ወይም ማንኛውም ብዙ እግሮች ያሉት - በምድር የሚሳብ እንስሳን ሁሉ፣ አትብሉ፤ እነዚህ ጸያፍ ናቸው፡፡
43በደረቱ በሚሳብ ማናቸውም ህያው ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፤ እነዚህ እናንተን ያረክሳሉ፡፡
44እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ በምድር በሚንቀሳቀስ በማናቸውም አይነት እንስሳ ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
45እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱስ መሆን አለባችሁ፡፡
46ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በውሃ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ማናቸውም ህያዋን ፍጥረታት፣ እንዲሁም በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታት ህጉ ይህ ነው፤
47ንጹህ ባልሆኑና ንጹህ በሆኑት መካከል ልዩነት ለመፍጠር፣ እና በሚበሉ ህያዋን ነገሮችና በማይበሉ ህያዋን ነገሮች መሃል ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡’”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።