መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሰቆቃው ኤርሚያስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእግዚአብሔር የቁጣ በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።
2አባረረኝ፥ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ።
3በእርግጥ ሊቃወመኝ ወደ እኔ ዘወር አለ፥ ቀኑን ሙሉ እጁን በላዬ መለሰ።
4ሥጋዬንና ቆዳዬን ቀደደ፥ አጥንቶቼን ሰበረ።
5ቅጥር በዙሪያዬ ገነባብኝ፥ በምሬትና በመከራም ከበበኝ።
6ከሞቱ ረዥም ጊዜ እንደሆናቸው በጨለማ ስፍራ እንድኖር አደረገኝ።
7በዙሪያዬ ቅጥርን ገነባ፥ ማምለጥም አልችልም። የእግሬን ሰንሰለት አከበደ።
8ለርዳታ ብጮኽና ብጣራም ጸሎቴን ዘጋ።
9ከጥርብ ድንጋይ በተሰራ ቅጥር መንገዴን ዘጋ፤የምሄድብት የትኛውም መንገድ ጠማማ ሆን።
10መንገዴን ቀየረው።
11ገነጣጠለኝ፥ብቸኛም አደረገኝ።
12ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ።
13ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ። ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ። ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።
14ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ።
15ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።
16ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፥ ወደ መሬት ውስጥ ረገጠኝ።
17ሰላምን ከሕይወቴ አስወገድክ፤ ከእንግዲህ መቼም የትኛዉንም ደስታ አላስብም።
18ስለዚህም«ጽናቴ ጠፍቷል፥ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ተስፋዬም ሄዷል» አልሁ።
19መከራዬንና እሬትና ምሬት ወደ አለበት መጥፋቴን አስባለሁ።
20በእርግጥ አስበዋለሁ፥ተስፋ በመቁረጥ በውስጤ አቀረቀርኩ ።
21ነገር ግን ይህን አስባልሁ፥ ተስፋ ሊኖረኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው።
22ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና።
23የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!
24ለራሴ እንዲህ አልኩ «እግዚአብሔር ዕጣ ክፍሌ ነው» ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።
25ለምጠብቀው፥ ለምትፈልገውም ሕይወት እግዚአብሔር መልካም ነው።
26የእግዚአብሔርን ማዳን በዝምታ መጠበቅ መልካም ነው።
27በወጣትነቱ ቀንበርን ቢሸከም ለሰው መልካም ነው።
28እግዚአብሔር አሸክሞታልና ለብቻው ይቀመጥ ዝምም ይበል።
29ምናልባት ተስፋ ሊኖር ይችላልና አፉን በአፈር ዉስጥ ያኑር።
30ለሚመታው ጉንጩን ይስጥ። ዉርደትንም ይጥገብ፤
31እግዚአብሔር ለዘላለም አይጥለውምና!
32ሐዘንን ቢያመጣም እንኳን ከታላቁ የኪዳኑ ታማኝነት በሚሆን ርኅራኄ ይራራል።
33ምክንያቱም ከልቡ አይጨቁንም፥ወይንም የሰዎችን ልጆች አያሰቃይም።
34በምድር ያሉ ምርኮኞችን ሁሉ ከእግሩ በታች ሲያደቅቅ፥
35በልዑል ፊት የሰውን ፍርድ ሲያጣምም፥
36ፍትህ ፈላጊውን ሲያፍን- ጌታ አያይምን?
37ጌታ ካላዘዘው በቀር የሚናገርና የሚፈጽመው ማን ነው?
38ጥፋትና ስኬት ከልዑል አፍ የሚወጡ አይደሉምን?
39ታዲያ ማንም ሕያው የሆነ ሰው እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? ማንም ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል?
40መንገዳችንን እንፈትን እንመርምርም፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
41ልባችንንና እጃችንን በሰማይ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣና እንዲህ ብለን
42እንጽልይ፦ተላልፈናል በአንተም ላይ ዐምፀናል፥ስለዚህ ይቅር አላልከንም።
43ራስህን በቁጣ ሸፈንክ አሳደድከንም። አረድከን፥ አራራህልንምም።
44ራስህን በደመና ሸፈንክ፥ስለዚህም ማለፍ የሚችል ጸሎት የለም።
45በአሕዛብም መካከል ቆሻሻና ውዳቂ አደረግኽን ።
46ጠላቶቻችን በእኛ ላይ በማላገጥ አፋቸውን ከፈቱ።
47የአሳር ጉድጓድ ፥የባዶነትና የጥፋት ፍርሃት መጣብን።
48ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ዓይኔ ያለማቋርጥ ውኃ አፈሰሰች።
49ዓይኖቼ ያፈሳሉ አያቆሙምም፥ለለቅሷቸውም ፍጻሜ የለውም፥
50እግዚአብሔር ውደ ታች እስኪመለከት ከሰማይም እስኪያይ ድረስ።
51ከከተማዬ ሴቶች ልጆች የተነሳ ዓይኔ ጽኑ ስቃይ በሕይወቴ ላይ አመጣች።
52ጠላቶቼ ያለ ምንም ምክንያት፥ያለመታከት እንደ ወፍ አደኑኝ።
53ሕይወቴን በጉድጓድ ዉስጥ አጠፉ፥ ድንጋይንም በላዬ ከመሩ።
54ውኆች በራሴ ላይ አለፉ፤እኔም፦ «ተቆርጬአለሁ!» አልኩ።
55እግዚአብሔር ሆይ፥ ከጥልቅ ጉድጓድ ስምህን ጠራሁ።
56«እርዳታ ፈልጌ ስጮህ፥እረፍት ፈልጌ ስጣራ ጆሮህን አትሰውር» ባልኩኝ ጊዜ ድምጼን ሰማህ።
57በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቀርበህ «አትፍራ» አልከኝ።
58ጌታ ሆይ በተከሰስሁ ጊዜ ስለ ነፍሴ ተሟገትህ፤ ሕይወቴንም አዳንክ።
59እግዚአብሔር ሆይ እንዴት እንደ ጨቆኑኝ አይተሃል፥ ክርክሬን በጽድቅ ፍረድልኝ።
60በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉ፥የበቀላቸውን ሥራ ሁሉ አይተሃል።
61እግዚአብሔር ሆይ በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉና እሽሙጥጫቸውን ሰምተሃል።
62በእኔ ላይ የተነሱብኝን ከንፈሮች ሰምተሃል፤ቀኑን ሁሉ እኔን በመቃወም የሚያስቡትን ጥልቅ አሳቦች ሰምተሃል።
63እግአብሔር ሆይ! ተመልከት፥ በመቀመጣቸውም ሆነ በመነሳታችው የስላቅ ዘፈናቸው ምክንያት ነኝ።
64እግዚአብሔር ሆይ እጆቻቸው እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንደዚያው መልሰህ ክፈላቸው።
65ፍርሃትን በልባቸው አድርግ፥ ርግማንህንም በላይቸው አድርግ።
66እግዚአብሔር ሆይ! በቁጣህ አሳድዳችው፥ከሰማይት በታች በየስፍራው አጥፋቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።