1ከዚያም በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቆላማው በታላቁ ባሕር ዳርቻ በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም
2ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።
3የገባዖን ሰዎችም ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥
4እነርሱ ደግሞ የማታለል ዕቅድ አደረጉ። ራሳችውን እንደ መልእክተኛ አድርገው ቀረቡ። ያረጀና የተቀደደ ጆኒያ ወስደው በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ። ደግሞም ያረጀ፥የተቀደደና የተሰፋ አሮጌ ወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ።
5ያረጀ የተሰፋም ጫማ በእግራቸው አደረጉ፤ አሮጌምና የተቀደድ ልብስም ለበሱ። ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ።
6ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሕዝብ፦በጣም ሩቅ አገር ከሆነ ተጉዘን የመጠን ነን፥ ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።
7የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያንን፦ ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ ትሆናላችሁ። እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን? አሉአቸው።
8እነርሱም እንዲህ አሉት፦ እኛ የእናንተ አገልጋዮች ነን። ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?
9እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ አሉት፦ እኛ አገልጋዮችህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር እዚህ መጥተናል። ዝናውንም በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥
10በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን በንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።
11ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፦ ለጉዞአችሁም ስንቅ በእጃችሁ ያዙ። ልትገናኙአቸውም ሂዱና እንዲህ በሉአቸው፦ እኛ አገልጋዮቻችሁ ነን፤ ከእኛም ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ።
12ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩስን ለስንቅ ከቤታችን የወሰደነው ነው። ነገር ግን ተመልከቱ፥ አሁንም ደረቅና የሻግብተ ነው።
13እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል። ጉዞአችንም እጅግ ሩቅ ስለ ነበረ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።
14እስራኤላውያንም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔርም ምክርን አልጠይቁም ነበር።
15ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የማኅበሩም አለቆች ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።
16የእስራኤላውያንም ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፥ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ዐወቁ።
17ከዚያም እስራኤላውያን ተዘጋጅተው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ። የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ክፈራ፥ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ናቸው።
18የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን አድርገው ስለነበረ እስራኤላውያንም ጥቃት አልደረሱባቸውም። የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጉረመረሙ፥
19ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ አሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን ስለገባንላቸው አሁን ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም፥
20የምናደርግላቸው ነገር ቢኖር ይህ ነው፦ የገባንላቸውን የቃል ኪዳን ማሐላ ብናፈርስ ቁጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ነው። የሕዝቡም አለቆች ለሕዝባቸው እንዲህ አሉ፦ በሕይወት ይኑሩ።
21ስለዚህም የእስራኤል አለቆች ስለእነርሱ እንደ ተናገሩት ገባዖናውያን ለእስራኤላውያን ሁሉ እንጨት ሰባሪና ውኃ ቀጂ ሆኑ።
22ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እዚሁ በመካከላችን እየኖራችሁ፥ ከእናንተ ሩቅ ስፍራ ነው የመጠነው፥ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው?
23ስለዚህ በዚህ ምክንያት እናንተ የተረገማችሁ ናችሁ፥ አንዳንዶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ሁል ጊዜ እንጨት ሰባሪና ውኋ ቀጂ አገልጋዮች ትሆናላችሁ።
24እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ እግዚአብሔር አምላክህ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው፥ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በእርግጥ ለእኛ አገልጋዮችህ ተነግሮናል፥ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይውታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል።
25እነሆ አሁን በእጅህ ነን፥ መልካምና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።
26ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች እጅ አዳናቸ እስራኤላውያንም አልገደሏቸውም።
27በዚያም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ሰባሪችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው።