መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራ አትደንግጥ። ጦረኞችንም ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ። ተመልከት፥ የጋይን ንጉሥ፥ ሕዝቡን፥ ከተማውንና ምድሩን በእጅህ ሰጥቼሃለሁ።
2በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ ምርኮውንና ከብቱን ግን ለራሳችሁ ትወስዳላችሁ። ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አዘጋዝጅ አለው።
3ኢያሱም ተነሣና ጦረኞቹንም ሁሉ ወደ ጋይ ወሰዳቸው። ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መርጦ በሌሊትም ሰደዳቸው።
4እንዲህም ብሎ አዘዘቸው፦ እነሆ፥ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ። ከከተማይቱ በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ነገር ግን ሁላችሁም ተዘጋጁ።
5እኔና ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን። እንደ በፊቱ ሊያጠቁን በሚመጡበት ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን።
6አስቀድመን እንደ ሸሸን፥ የምንሸሸ ይመስላቸዋል፥ ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል። እንዲህም ይላሉ፦ባለፈው እንዳደረጉት ከፊታችን እየሸሹ ነው። እኛም ከእነርሱ እንሸሻለን።
7እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ መጥታችሁ ከተማዋን ትይዛላችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁም እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል።
8ከተማይቱንም በያዛችኋት ጊዜ በእሳት አቃጥሉአት። በእግዚአብሔርም ቃል እንደታዘዛሁ ታደርጋላችሁ። እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።
9ኢያሱም ሰደዳቸው፤ እነርሱም ወደሚደበቁበት ስፍራ ሄደው፥ በጋይና በቤቴል መካከልም ከጋይ በስተምዕራብ ተደበቁ። ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።
10ኢያሱም ማልዶ ተነሣና ሕዝቡን አሰለፈ፤እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች የጋይን ሕዝብ አጠቁ ።
11ከእርሱም ጋር የነበሩ ጦረኞች ሁሉ ሄደው፥ ወደ ከተማይቱ ደረሱ። ወደ ከተማይቱ አጠገብ መጡና በሰሜን በኩል በጋይ ሰፈሩ። በእነርሱና በጋይ መካከል ሸለቆ ነበረ።
12አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል በድብቅ አስቀመጣቸው።
13በከተማይቱ የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ፤ በከተማይቱ ሰሜን በኩል ዋና ጦርና በከተማይቱ ምዕራብ በኩል ደጀን ጦር ጠባቂዎችን አኖሩ። ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው አደረ።
14የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ ይህ ስለታወቀ፥እርሱና ሠራዊቱ በማለዳ ተነስተው እስራኤልን ለማጥቃት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ወዳለው ሰፍራ ቸኮሉ። ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር ለማጥቃት እንዳለ አያውቅም ነበር።
15ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ራሳቸው በፊታቸው ድል የተነሡ መስለው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ።
16በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ በአንድነት ከኋላቸው እንዲሄዱ ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም ርቀው ወጡ።
17በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም። ከተማይቱንም ክፍት አድርገው፥ እስራኤልን አሳደዱ።
18እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእጅህ ያለውን ጦር በጋይ አነጣጥር፤ ጋይንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ።
19የተደበቁትም ሠራዊት ፈጥነው ከስፍራቸው ወጥተው ኢያሱም እጁን እንደ ዘረጋ ሮጡ። ወደ ከተማይቱም ሮጡ፤ ገብተውም ያዙአት። ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።
20የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ተመለከቱ። ከከተማይቱ ወደ ሰማይ የሚወጣውን ጢስ አዩ፤ ወዲህ ወይም ወዲያም መንገድ ማምለጥ አልቻሉም። ወደ ምድረ በዳ ሸሽተው የነበሩ የእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ያሳድዱአቸው የነበሩትን ለመግጠም ተመለሱ።
21ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ድብቅ ጦር ከተማይቱን እንደ ያዙ ወደ ላይ ከሚወጣ ጢስ ጋር ባዩ ጊዜ፥ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ።
22ሌሎቹም ወደ ከተማይቱ ሄደው የነበሩ የእስራኤል ሠራዊት ለማጥቃት ወጡ። ስለዚህም የጋይ ሰዎች በእስራኤል ሠራዊት መካከል ሌሎቹ በዚህ በኩልና ሌሎቹ በዚያ በኩል ተያዙ። እስራኤልም የጋይን ሰዎች አጠቁአቸው፤ አንዳቸውም አልተረፉም፤ አላመለጡምም።
23በሕይወት የያዙትን የጋይንም ንጉሥ ማርከው ወደ ኢያሱ አመጡት።
24እንዲህም ሆነ፤ የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ አጠገብ እስራኤልን ሲያሳድዱ በነበሩበት ቦታ ሁሉም የመጨረሻ በሰይፍ ስለት እስኪ ወድቁ ድረስ ጨርሰው ከገደሉአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ። በሰይፍም ስለት መቱአቸው።
25በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት የወደቁት ወንዶችና ሴቶች የጋይ ሰዎች ሁሉ አሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ።
26ኢያሱም የጋይን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም።
27እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ለራሳቸው ወሰዱ።
28ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን አደረጋት። እስከ ዛሬም ድረስ ባዶ ስፍራ ሆነች።
29የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው። ኢያሱም ፀሐይ በገባች ጊዜ የንጉሡን አስክሬን ከዛፍ አወርደው፥ በከተማይቱ በር አደባባይ እንዲጥሉት አዘዘ። በላዩም ታላቅ የድንጋይ ክምር አደረጉት። እስከ ዛሬ ድረስም ይህ የድንጋይ ክምር አለ።
30ከዚያም ኢያሱ በጌበል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
31የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዳዘዘ፦ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረ ድንጋይና ብረት ካልነካው ነበረ። በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ።
32የእስራኤልም ሰዎች ፊት በድንጋዮቹ ላይ የሙሴን ሕግ ቅጂ ጻፈባቸው።
33እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ በመጻተኞችና በአገሩ ልጆች ፥እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በካህናትና በሌዋውያን ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘ፥የእስራኤልን ሕዝብ አስቀድሞ ባረኩ።
34ከዚህም በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ እንደ ተጻፉ የሕጉን ቃሎች ሁሉ በረከቱንና እርግማኑን አነበብ።
35ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በሴቶቹም፥ በሕፃናቱም፥ በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል ሳያስቀር ሁሉን አነበበ ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።