መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶነጼዴቅ ኢያሱ ጋይን ይዞ ፈጽሞ እንደ ደመሰሳት፤ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤል ጋር እንዴት የሰላም ውል አድርገው በመካከላቸው መኖራቸውን ሰማ።
2የኢየሩሳሌም ሕዝብ ፈሩ፥ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ ነች። ገባዖንም ከጋይ ይልቅ ትልቅና ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።
3ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፥ ወደ የኬብሮን ንገሥ ሆነም፥ ወደ የያርሙት ንጉሥ ጲርአም ፥ ወደ የለኪሶ ንጉሥ ያፈዓና ወደ የዔግሎን ንጉሥ ዳቤር ላከ።
4ወደዚህ መጥታችሁ አግዙኝ። ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ስላደረጉ ገባዖንን እንምታ።
5ከዚያም አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን ሠራዊታቸውን ሁሉ አስተባብረው፥ ገባዖንን ወጓት።
6የገባዖንም ሰዎች ወደ ኢያሱና ወደ ጌልገላ ሠራዊት መልእክት ላኩ። እንዲህም አሉ፦ ከአገልጋዮቻችሁ እጃችሁን አታውጡ ፍጠኑ። በፍጥነት መጥታችሁ አድኑን። በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እኛን ለማጥቃት ተሰልፈውብናልና እርዱን። እኛን ባሮችህን አትተወን ርዳን ፈጥነህ በመድረስም አድነን ብለው ላኩበት።
7ስለዚህ ኢያሱ እርሱና ተዋጊዎች ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ጨምሮ ከጌልገላ ወጣ።
8እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራቸው። በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ማንም ሊቋቋሙህ አይችልም።
9ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት ደረሰባቸው።
10እግዚአብሔም የጠላትን ሠራዊት በእስራኤል ፊት ግራ አጋባቸው። እጅግ መታቸው። በገባዖንም ወደ ቤት ሖሮን በሚያስወጣው መንገድ እስከ ዓዜቅ መንገድ እስከ መቄዳም ድረስ ተከትሎአቸው አሳድዶ መታቸው።
11ከቤት ሖሮን ወደ ዓዜቃ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሽሹበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ ድንጋዮች ወረወረባቸው ሞቱም። በእስራኤል ሰዎች ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋዮች የሞቱት የበለጡ ነበሩ።
12ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በአሞራውያን ላይ ድል በሰጠበት ዕለት ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ። ኢያሱም በእስራኤል ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ "ፀሐይ፥ በኤሎን ሸለቆ በገባዖን ላይ ይቁም።"
13ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪ በቀል ድረስ፤ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፥ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ላይ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይ በሰማዩ መካከል ቆመች፥ ለሙሉ ቀን ያህል አልተንቀሳቀሰችም ነበር።
14እግዚአብሔር የሰውን ቃል እንደዚያ የሰማበት ዕለት ከዚያ በፊት ወይም ከዚያ በኋላ አልነበረም። እግዚእአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበር።
15ኢያሱና መላው እስራኤል ወደ ጌልገላ ሰፈር ተመለሱ።
16በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን ገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ራሳቸውን ደብቀው ነበር።
17ኢያሱም አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ሰማ፤
18ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባልሉ፤ወታደሮችንም እንዲጠብቁአቸው በዚያ አቁሙ። ቸልም አትበሉ።
19ጠላቶቻችሁን አሳዱአቸው፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም ጥቃት አድርሱባቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ አድርጉአቸው።
20ኢያሱና እስራኤል ልጆች ፈጽሞ እስኪያጠፉ ድረስ ከታላቅ ጭፍጨፋ ጋር ጨረሱ። የተረፉት ጥቂቶቹ ብቻ ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ደረሱ።
21ከዚያም ሠራዊቱ በሙሉ በደኅና ተመልሶ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ ተመለሰ። በእስራኤላውያንም ላይ አንድት ቃል ለመናገር ማንም ሰው የደፈረ አልነበረም።
22ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ የዋሻውንም አፍ ክፈቱና ከዋሻው እነዚህን አምስቱን ነገሥታት አምጡልኝ።
23እነርሱም እንዳለው አደረጉ። እነዚህንም አምስቱን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንን ንጉሥ፥ የያርሙትን ንጉሥ የለኪሶን ንጉሥና የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት።
24እነዚህን ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባማጡበት ጊዜ፥ እርሱም እያንዳንዱን የእስራኤል ሰዎች ጠራቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን የጦር አዛዦችን እንዲህ አላቸው፦ እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት አንገት ላይ አድርጉ። እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግሮቻቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ አሳረፉ።
25ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። በርቱ፥ ጽኑም። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምትዋጉበት ጊዜ በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲህ ያደርጋል።
26ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው። በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው። አስክሬናቸውም እስኪመሽ ድረስ ተሰቅለው ነበር።
27የፀሐይ መጥለቂያ በሆነ ጊዜ ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፦ ከዚያም የነገሥታቱን አስክሬኖች ከዛፎቹ ላይ እንዲያወርዱ ቀድሞ ራሳቸውን ደብቀው ወደነበሩበት ዋሻ ውስጥ እንዲጥሉአቸው አዘዛቸው። በዋሻውም አፍ ላይ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ። እነዚያ ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
28በዚህ መንገድ በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከንጉሥዋም ጭምር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ። በሕይወት ያሉትንም ፍጥረት ሁሉ ምንም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋቸው። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፥ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።
29ኢያሱና እስራኤላውያን ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ። ወጓትም።
30እንደገናም ከልብና ጋር ጦርነት ገጠሙ። እግዚአብሔርም ከተማይቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱም በተከማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ። ሕይወት ያለውን ምንም አላስቀረም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ።
31ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከእርሱ ጋር ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ። በእርስዋም ሰፈሩ፤ ጦርነትም አደረጉ።
32እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠው። ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት። በልብና እንዳደርገው በሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ።
33ከዚያ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ። ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ እርሱንና ሕዝቡን መታቸው።
34ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶን ወደ ዔግሎን አለፉ። እዚያም ሰፈሩ፤ ወጓትም፤
35በዚያኑ ዕለት ከተማዋንም ያዟት። ኢያሱም በለኪሶ እንዳደረገ ከተማይቱንና በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው በሰይፍ ስለት አጠፏት።
36ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከዔግሎን ወደ ኬብሮን አለፉ። በከተማይቱም ጦርነት አደረጉ።
37ከተማዪቱንም ከንጉሥዋ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጭምር ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። በዔግሎን እንዳደርጉት ሁሉ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። ማንኛውንም ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ አጠፋ።
38ከዚያ ኢያሱና እስራኤል ሠራዊት ከእርሱ ጋር ወደ ኋላ ተመልሰው በደቤርን አለፉ፤ ጦርነቱንም አደረጉ።
39ከተማዪቱን ንጉሥዋንና በአካባቢ ያሉ መንደሮቿን ሁሉ ያዙ። ከተማይቱንና በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ፥ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። ኢያሱ በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ በዳቤርና በንጉሥዋ ላይ አደረጉት።
40ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌቭን ቆላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋር አሸነፈ። ከነገሥታቱንም ያስቀረው ማንም የለም። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረትሕይወት ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው።
41ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ፥ የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ አጠፋ።
42ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን የያዘው በአንድ ጊዜ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ስለተዋጋ ነው።
43ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።