መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል ሕዝብ ግን እንዲጠፉ ከተለዩ ነገሮች በመውሰድ ታማኝነትን አጎደሉ። ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች ወስደ፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ።
2ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤት አዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ላከ። እርሱም፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው። ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።
3እነርሱም ወደ ኢያሱ ተመልሰው፡- ሕዝብን ሁሉ ወደ ጋይ አትላክ። ጋይን እንዲመቱ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ይላክ። የጋይ ሰዎች በቁጥር ጥቂቶች ስለሆኑ ሕዝብ ሁሉ በውጊያ እንዲደክም አታድርግ።
4ከሠራዊቱ ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ወደዚያ ወጡ፤ እነርሱም ከጋይ ሰዎች ፊት ሸሹ።
5የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን መቱ፥ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው፤ በቁልቁለቱም መቱአቸው። የሕዝቡም ልብ ፈራ፤ ድፍረትንም አጡ።
6ኢያሱም ልብሱን ቀደደ። እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድርስ በግምባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
7ኢያሱም አለ፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ ይህን ሕዝብ ቀድሞኑ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? እንዲያጠፉን በአሞራውያን እጅ ለምን አሳልፈህ ሰጠሃን? ከዚህ የተለየ ምርጫ ማድረግ በቻልንና በዮርዳኖስም ማዶ በተመቀመጥን ይሻለን ነበር።
8ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት ከሸሹ በኋላ ምን ማለት እችላለሁ?
9ይህንን ከነዓናውያንና በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ይሰማሉ። እነርሱም ይከብቡናል፥ በምድር ያሉትም ሕዝብ ስማችን እንዲረሳ ያደርጋሉ። ለታላቁ ስምህስ የምታደርገው ምንድን ነው?
10እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ተነስተህ ቁም! ለምን በግምባርህ ተደፍተሃል?
11እስራኤል ኃጢአትን አድርጎአል። ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል። ለጥፋት ከተለዩት ነገሮችን ሰርቀዋል፤ ሰርቀው የወሰዱትንም ኃጢአት በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።
12በዚህም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም። ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነው በጠላቶቻቸው ፊት ሸሹ። በመካከላችሁ እስካሁን ያለውን መወገድ ያለበትን እርም ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኃላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
13ተነሣና ሕዝቡን ቀድስልኝ፤ እንዲህም በላቸው፦ራሳችሁን ለነገ ለእግዚአብሔር ቀድሱ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ እስራኤል ሆይ ፥ሊጠፉ የሚገቡ ነገሮች እስካሁን በመካከላችሁ አለ። መጥፋት ያልባቸው ነገሮች ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።
14ነገም ራሳችሁን በየነገዳችሁ ታቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም በዕጣ የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ አንድ በአንድ ይቀርባል።
15ለጥፋትም የተለየ ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በማፍረሱና በእስራኤልም ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ በማድረጉ እርሱና ለእርሱም ያለው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠላል።
16ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ።
17የይሁዳንም ወገን አቀረበ፥የዛራም ወገን ለየ። የዛራንም ወገን እያንዳንዱን አቀረበ፤ ዘንበሪም ተለየ።
18የቤተ ሰቡንም እያንዳንዱን አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።
19ከዚያ ኢያሱ አካንን አለው፦ ልጄ ሆይ፥ በእስራኤልም አምላክ ፊት እውነቱን ተናገር፥ ለእርሱም ተናዘዝ። ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ ከእኔም አትሸሽግ።
20አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ። ያደረግሁትም ይህንን ነው፦
21በዘረፋ መካከል አንድ የሚያምር የባቢሎን ኮት፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም። እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው አለው።
22ኢያሱም መልእክተኞችን ሰደደ፥ ወደ ድንኳኑም ሮጡ፤ ዕቃዎቹም ነበሩ። በድንኳኑም ውስጥ ተሸሽጎ አገኙት ብሩም ከበታች ነበረ።
23ከድንኳኑም መካከል ዕቃዎቹን ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጡት። በእግዚአብሔርም ፊት አኖሩት።
24ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ኮቱንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያውዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው።
25ኢያሱም እንዲህ አለው፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔርም ዛሬ ያስጨንቅሃል። እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ሁሉንም በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።
26በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ሆነ። እግዚአብሔርም ከቁጣው ትኩሳት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።