መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእስራኤልም ሠራዊት የተነሣ የኢያሪኮ በሮች መጽሞ ተዘግተው ነበር። ወደ እርስዋም የሚገባና የሚወጣ ማንም አልነበረም።
2እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን የሠለጠኑ ወታደሮችዋንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ።
3ሠራዊቶኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ መዞር አለባቸው። ይህንንም ለስድስት ቀናት አድርጉት።
4ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
5ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ የመለከቱንም ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኽ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል። እያንዳንዱ ወታደር ወደፊት በመሄድ ማጥቃት አለባቸው።
6ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው።
7ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ሠራዊቱም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።
8ኢያሱም ለሕዝቡ እንደተናገረው ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይዘው ወደፊት እያለፉ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ከኋቸው ይከተላቸው ነበር።
9ሠራዊቱም በካህናቱ ፊት ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ ይሄዱ ነበር፤ ከዚያም ከቃል ኪዳን ታቦት ኋላ ደጀን ጦር ይሄድ ነበር፤እንዲሁም ካህናቱ ቀንደ መለከታቸውን ያለማቋረጥ ይነፉ ነበር።
10ኢያሱ ግን ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እኔ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ከአፋችሁም ድምፅ አይውጣ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ ትጮኻላችሁ።
11ስለዚህ እግዚአብሔር የዚያን ቀን የቃል ኪዳን ታቦት አንድ ጊዜ ከተማይቱን እንዲዞር አደረገው፤ ከዚያም ወደ ማደሪያቸው ገቡ፤ ሌሊቱንም እዚያው አደሩ።
12ከዚያም ኢያሱ ማለዳ ተነሣ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸከሙ።
13ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በቀስታ እየሄዱ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። ሠራዊቱም በፊታቸው ይሄዱ ነበር። የደጀን ጦር ከእግዚአብሔር ታቦት ኋላ በሚድበት ጊዜ የቀንደ መለከት ድምፅ ያልማቋረጥ ይሰማ ነበር።
14በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲሁ አደረጉ።
15በሰባተኛውም ቀን ሲነጋ ማልደው ተነሡ፥ ከዚህ በፊት በተለመደው ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩት በዚያ ቀን ነው።
16በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን አዘዘ፦ እግዚአብሔር ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።
17ከተማይቱና በእርስዋም ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየና ለጥፋት ይሆናሉ። የላክናቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ብቻና ከእርስዋም ጋር በቤትዋ ውስጥ ያሉት ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ።
18እናንተ ግን ለጥፋት የተለዩ ነገሮችን ከለያችሁት በኋላ አንዳች እንዳትወስዱ ራሳችሁን ጠብቁ። ለጥፋትም ከሆነው ነገር አንዳች የወሰዳችሁ እንደ ሆነ የእስራኤልን ሰፈር እንዲጠፋ ታደርጉታላችሁ፥ ችግርም ታመጣላችህ።
19ብር፥ ወርቅ፥ ናስና ከብረት የተሠሩ ዕቃዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።
20ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ። ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታልቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ሲወድቅ፤ ሕዝቡም እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፤ ከተማይቱንም ያዙ።
21በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም ፥በጉንና አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
22ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት ግቡ ከዚያም ሴቲቱንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ።
23ሰላዮቹም ወጣቶች ሄደው ረዓብን አውጧአት፤ አባትዋንና እናትዋን፥ ወንድሞችዋንም፥ አብሯት የነበሩ ቤተ ዘምዶችዋንም ሁሉ አወጡ። ከእስራኤልም ሰፈር ውጭ ወዳለው ስፍራ አመጦአቸው።
24ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። ብሩ፥ ወርቅ፥የናሱና የብረት ዕቃዎች ብቻ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አስቀመጡአቸው።
25ነገር ግን ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውን መልክተኞች የሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥አብሯት የነበሩትንም ሁሉ ኢያሱ በሕይወት እንዲሆሩ ፈቀደላቸው። እርስዋም ኢያሱ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ የላካቸውን ሰዎች ስለሸሸገች በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ትኖራለች።
26በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ ይህችን ኢያሪኮ ከተማን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን። መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይሙት፥ እርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይሙት፥ ብሎ ማለ።
27እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።