1በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በታላቁም ባሕር አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ የዮርዳኖስን ውኃ እግዚአብሔር እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ሕዝብ የተነሣ የአንድም ሕዝብ ነፍስ አልቀረላቸውም።
2በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦"የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርተህ የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና ግርዛቸው።"
3ኢያሱም የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርቶ ግብት ሃራሎት (ትርጉሙም የግርዛት ኮረብታ) በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ወንዶች ሁሉ ገረዛቸው።
4ኢያሱም የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ከግብፅ የወጡት ወንዶች ሁሉ ጦረኞችን ሁሉ ጭምር ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ።
5የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር።
6ከግብፅ የወጡ የእስራኤል ሕዝብና ጦረኞች ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው እስኪሞቱ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይጓዙ ነበር ። እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው ማለላቸው።
7እግዚአብሔር በእነርሱ ፋንታ ያስነሳቸው በመንገድ ሳሉ ሳይገረዙ የነበሩ ኢያሱም ገረዛቸው እነዚህን ልጆቻቸው ነበሩ።
8ሕዝቡም ሁሉ በተገዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ነበሩ።
9እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ይጠራል።
10የእስራኤልም ሕዝብ በጌልገላ ሰፈሩ። ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።
11ከፋሲካውም በዓል ቀን በኋላ በዚያው ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ቂጣና ቆሎ በሉ።.
12ከምድሪቱም ፍሬ ከበሉበት ቀን በኋላ መና ተቋረጠ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለእስራኤል ልጆች መና አልነበራቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።
13ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ አጠገብ በነበረ ጊዜ ዓይኖቹን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው።
14እርሱም፦ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ እዚህ መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው? አለው።
15የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።