1ከብዙ ቀናት በኋላ፥እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ፥ ኢያሱ ሸምግሎ ነበር።
2ኢያሱም እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እኔ በጣም ሸምግያለሁ።
3እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።
4ተመልከቱ! እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ መድቤላችኋለሁ።
5እግዚአሔር አምላካችሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ይበትናቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።
6ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።
7በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም።
8እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ተጣበቁ።
9እግዚአብሔርም ታላላቆችንና ኃይለኞችን መንግሥታት ከፊታችሁ አስወጣላችሁ። እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።
10እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተጋገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና፥ ከእናንተ አንድ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።
11እግዚእብሔር አምላካችሁን ትወድዱት ዘንድ ትኩረት አድርጉ።
12እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር ብትጣበቁ፥ወይም ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ ወይም እናንተ ወደ እነርሱም ወደ እናንተ ኅብረት ብታደርጉ፥
13ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እነዚህን ሰዎች እንደማያስወጣችሁ በርግጥ እወቁ። በዚህ ፈንታ ከዚህች እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ለእናንተም መውደቂያና ወጥመድ፥ በጎናችሁም መግረፊያ፥ በዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል።
14እነሆም ዛሬ የምድርን መንገድ ሁሉ እሄዳለሁ፤ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፥ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም።
15እግዚአብሔ አምላካችሁ የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።
16የእግዚአብሔር አምላካችሁን ቃል ኪዳን ብታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣትችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።