1በዚያን ጊዜም ኢያሱ የሮቤል ልጆችንና የጋድ ልጆችን የምናሴንም ነገድ እኩሌታ ጠራቸው።
2እንዲህም አላቸው፦ የእግዚእአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ጠብቃችኋል፥ እኔም ላዘዝኋችሁ ነገር ሁሉ ታዝዛችኋል።
3ይህንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፥ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃችኋል።
4አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራቸው ወድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል። አሁን እንግዲህ ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።
5የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ወደ እርሱም ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ ብቻ እጅግ ተጠንቀቁ።
6ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።
7ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕብብ ወንን በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በሰደዳቸው ጊዜ
8እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦ በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።
9የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓን በሴሎ ትተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ ሄዱ።
10በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዩርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
11ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርውዋል፤ የሚል ወሬ ደረሰላቸው።
12የእስራኤል ሕዝብ ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበስቡ።
13የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መልእክት ላኩ። የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ደግሞ ላኩ፥
14ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበሩ።
15በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ግድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መጡ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩአቸው፦
16የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት ኃጢአት ምንድን ነው? ዛሬ እግዚእአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋል ዛሬም በራሳችሁ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል።
17በፌጎር ያደረገነው ኃጢአታችን አይበቃምን? እስከ ዛሬም ድረስ ከዚያ ኃጢአት ራሳችንን አላነጸንበትም። ከዚያም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ።
18እናንተ ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል መመለስ ይገባችኋልን? ዛሬ በእግዚአሔር ላይ ብታምፁ ነገ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ይቆጣል።
19የርስታችሁም ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ። ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔርና በእኛ ላይ አታምፁ።
20የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአት ብቻውን አልሞተም።
21ከዚያም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦
22ሁሉን የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ታላቁ አምላክ እግዚአብሔር እርሱ ያውቃል፥ እስራኤልም እንዲያውቅ ያደርጋል! በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን እግዚአሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን
23መሥዋዕትና የእህልን ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅነትትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን።
24ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችንን፦ እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?
25እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአል። እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም ይሉአቸዋል ብለን ይህን አደረግን። በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከመፍራት ያስተዋቸዋል።
26ስለዚህ፦ መሠዊያ እንሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፤
27ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንት የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።
28ስለዚህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን፥ ይህን እንላለን እኛ፦ እነሆም አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዪ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕታችን ስለሌላ መሥዋዕት አይደለም። በማደሪያው ፊት ካለው ከአምላካችን
29ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።
30ካህኑ ፊንሐና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር ከነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው።
31የካህኑም በአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው።
32የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው።
33ነገሩም የእስራኤል ልጆችን ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው አንዲወጉአቸው አልተናገሩም።
34የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።