መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 24

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበስበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠራቸው፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።
2ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።
3አባታችሁንም አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወስጄ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም በልጁ በይስሐቅ በኩል እንዲበዛ ሰጠሁት።
4ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት። ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ነገር ግን ያዕቆብና ልጂቹ ወደ ግብፅ ወረዱ።
5ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ ግብፃውያንን በመቅሠፍት መታሁ። ከዚያም በኋላ አወጣኋችሁ።
6አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋችው፤ ወደ ባሕሩም መጣችሁ። ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አሳደዱአቸው።
7አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ። ባሕሩንም በእነርሱ ላይ መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም። ዓናኖቻችሁም በግብፃውያን ላይ ያደረግሁትን አይታችኋል። ለረጅም ጊዜም በምድረ በዳ ተቀመጣችሁ።
8እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ። ከእናንም ጋር ተዋጉ፥ በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ። ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።
9-10የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተንሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።እኔ ግን በለዓምን አልሰማሁትም። እርሱም በዚህ ፈንታ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ።
11ዮርዳኖስንም ተሻግራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ። የኢያሪኮም ሰዎች፥ ከአሞራዊውያን፥ ከፌርዛዊውያን፥ ከከነዓናዊውያን፥ ከኬጢያዊውያን፥ ከጌርጌሳዊውያን፥ ከኤዊያዊውያንና ከኢያቡሳዊውያን፥ ጋር ተዋጉአችሁ። በእነርሱም ላይ ድልን ሰጠኋችሁ፤አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ።
12በፊታችሁ ያሉትን ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት እንዲያስወጡአቸው በፊታችሁም ተርብን ሰደድሁባቸው። ይህም በእናንተ ሰይፍና ቀሥት አይደለም።
13ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ዛሬ የተቀመጣችሁባቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። ያልተከላችኋቸውን ወይንና ወይራ በላችሁ።
14አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በግብፅም ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ።
15እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን።
16ሕዝቡም መልሰው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርን ትተን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከእኛ ይራቅ፥
17እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባችውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።
18እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አስወጣ። ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እግዚአብሔርን እናመልካለን።
19ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ እርሱ ቅዱስና፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።
20እግዚአብሔርን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ያጠፋችኋል።
21ሕዝቡም ኢያሱን፦ እንዲህ አይሁን እግዚአብሔርን እናመልካለን አሉት።
22ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፦ እግዚአብሔርን እንድታመኩት እንደመረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው። እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ።
23እርሱም፦ አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶችን አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አዘንብሉ አላቸው።
24ሕዝቡም ኢያሱን፦ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን፥ አሉ።
25በዚያን ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። በሴምም አዋጅንና ሕግን አደረገላቸው።
26ኢያሱም እነዚህን ቃላት ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ። ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።
27ኢያሱም ለሕዝቡ፦ ተመልከቱ፥ የተናገረነውን ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል። እግዚአብሔር የተናገርነውን ሁሉ ሰምቶአል። እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው።
28ስለዚህም ኢያሱ ሕዝቡን ወደ እያንዳንዱ ርስት እንዲሄዱ አደረገ።
29ከዚህ ነገር በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሞልቶት ሞተ።
30በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምና ሴራ ቀበሩት።
31ኢያሱ በነረበት ዘመን ሁሉ፤ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አመለኩ።
32የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ የወጡት የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴም አባት ከኤሞር ልጆች በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት። እርሱም በአንድ መቶ ብር ገዛው፤እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።
33የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።