መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም የሌዋውያን ወገኖች አለቆች ወደ ካህኑ አልዓዘር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አለቆች ቀርቡ።
2እነርሱም በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ አሉአቸው፡- እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውንና ለከብቶቻችንም መሰማሪያ የሚሆኑ ከተሞች እንድትሰጡን አዞአችኋል።
3ስለዚህም የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚከተሉትን ከተሞች ለከብቶቻቸውም መሰማሪያ ጭምር እንዲሆኑ ርስታቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው።
4ለቀዓትም ወገኖች የዕጣው ውጤት እንዲህ ሆነ፦ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች፥ ከይሁዳ ነገድ ከስምዖንም ነገድ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጣቸው።
5ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድና ከምናሴ ነገድ እክኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተቀበሉ።
6ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴር ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳን ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጣቸው።
7ለሜራሪም ልጅች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድአሥራ ሁለት ከተሞ ተቀበሉ።
8እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዛቸው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።
9ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው እነዚህን ከተሞች ሰጡ።
10እነዚህ ከተሞች ከሌዊ ልጆች ነገድ የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ተሰጥቶአቸው ነበር። የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ወጥቶላቸው ነበር።
11እንደ ኬብሮን ተመሳሳይ ቦታ በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት አርባቅ (ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ) የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን የከብቶች መሰማሪያዋን ሰጡአቸው።
12የከተማይቱንም እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።
13ለካህኑም ለአሮን ልጆች ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማሪያዋን፥ ልብናን ከመሰማሪያዋን ጋር ሰጡ፤
14የቲርንና መሰማሪያዋን፥ ኤሽት ሞዓንና መሰማሪያዋን፥
15ሖሎንንና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፥
16ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት ሳሚስንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ነበሩ።
17ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥
18ዓናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንንና መሰማሪያዋን፤አራት ከተሞችን ሰጡ።
19ለአሮን ልጆች ለካህናት የተሰጡ ከተሞች ከመሰማሪያቸው ባጠቃላይ አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
20ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የተሰጣቸ ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ዕጣ ወጥቶላቸው ነበር።
21ለእነርሱም በኤፍሬም ተራራማ አገር ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥
22ቂብጻይምንና መስማሪያዋን፥ ቤት ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
23ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥
24ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
25ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
26ለቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች የተሰጡ ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸውን ጋር አሥር ከተሞችናቸው።
27ለሌሎች ሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማይያዋን ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
28ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥
29የያርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ለጋሪሶን ነገድ ሰጡአቸው።
30ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋን፥
31ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረአብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
32ከንፍታሌምም ነገድ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞትዶርንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ለጌድሶን ነገድ ሰጡአቸው።
33የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ከመሰማሪያቸው ጋር አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
34ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥
35ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።
36ለሜራሪ ነገድ ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰምሪያዋን፥
37ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።
38ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ከጋድም ነገድ በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንማ መሰማሪያዋን ሰጡ።
39ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን ሜራሪ ነገድ ደግሞ የተሰጡ ባጠቃላይ አራት ከተሞች ናቸው።
40ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ባጠቃላይ አሥራ ሁለት ከተሞች ነበሩ።
41በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ።
42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ በዚህ ዓይነት መንገድ ነበሩ።
43እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ። ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።
44እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው። ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
45እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።