መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
2ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፡
3ሳያውቅም ሰውን የገደለ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ለዩ። እነዚህም ከተሞች ከተገደለበት ከማንኛውም ከደም ተበቃይ የሚሸሹበት ቦታ ይሆኑላችኋል።
4ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማይቱ ሽማግሌዎች ጉዳዩን ያስረዳል። እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡታል።
5ሰው የሞተበትም ደም ተበቃዩ መጥቶ ለመበቀል ቢሞክር፥ የከተማውም ሰዎች ሰውየውን ለከተማው ባለሥልጣናት አሳልፈው መስጠት አይኖርባቸውም። ይህን ማድረግ የማይገባቸው እርሱ የገደለው ከዚህ በፊት ጥላቻ ሳይኖርና ሆነ ብሎ ባለመሆኑ ነው።
6በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያን ጊዜ ያለው በሊቀ ካህንነት የሚያገለግለው እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ። ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ፥ ሸሽቶ ከነበረበት ከተማ ወደ ከተማውና ወደ ቤቱ ይመለሳል።
7በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።
8ከዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፣ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ቶላንን ለዩ።
9ማንም ሰው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽና በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው። ይህም ሰው በማኅብሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።