መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 19

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ።
2እነርዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፤ ቤርሳቤህም ሤባ፥ሞላዳ፥
3ሐጸርሹዕል፥ ባለ፥ዔጼም፥
4ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥
5ቤትማርካቦት፥ ሐጸርሱሳ፥
6ቤተ ለባኦት፥ ሻሩሔን፤ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
7ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ ዓሻን፤ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤
8እስከ ባዕላት ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞችና ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
9ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ። የይሁዳም ልጆች ዕድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸ መካከል ወረሱ።
10ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ።
11ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ።
12ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎት ታቦር ዳርቻ ዞረ። ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ።
13ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ።
14ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ።
15ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
16የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
17አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
18ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ወደ ከስሎት፥ወደ ሱነም፥
19ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺአን፥ ወደ አናሐራት፥
20ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥
21ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋቢም፥ ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤት ጳጼጽ ደረሰ፤ ድንበሩም ወደ ብቦርና ወደ ሻሕጽይማ፥ ወደ ቤት ሳሚስ ደረሰ።
22የድንበራቸውም መውጫ ዮርዳኖስ ነበረ፤ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
23የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
24አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
25ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አዚፍ፥ አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤
26በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ።
27ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤት ዳጎን ዞረ፥ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት ዓሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ በስተ ግራ ቡልም ወደ ካቡል ወጣ።
28ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲኖናም ደረሰ።
29ድንበርም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤
30ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ። እነዚህም ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
31የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
32ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
33ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ።
34ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ከዚያም በደቡም በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳስም ወንዝ በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።
35የተመሸጉትም ከትሞች እነዚህ፦ ነበሩ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥
36አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥
37ቃዴስ፥ኤድራይ፥ ዓይንሐጽር፥ ይርአን፥
38ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤት ዓናት፥ ቤት ሳሚስ፤ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ያልተቆጠሩ።
39የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
40ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
41የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥
42ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥
43ተምና፥አቃሮን፥
44ኢልተቄ። ገባቶን።ባዕላት፥ ይሁድ፥
45ብኔንርቅ፥ ጋትሪሞ፥
46ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን።
47የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለመቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። ስምዋንም በአባቶታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠርአት።
48የዳን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸ እነዚህ ከትሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
49ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።
50በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት። ከተማውንም እንደ ገና ሠርቶ ተቀመጠበት።
51ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ነገዶችና የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። የምርሪቱንም ማከፋፈል ሥራ ጨረሱ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።