መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 18

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ። በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
2ከእስራኤልም ልጆች መካከል ያልተካፈሉ ሰባት ነገዶች ቀርተው ነበር።
3ኢያሱም ለእስራኤል ሰዎች አላቸው፦ የአባቶቻቸሁ እግዚአብሔር አምላክ የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ድረስ ቸል ትላላችሁ?
4ከየነገዱም ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ። ተነሥተውም የምድሪቱን ላይና ታች ይለካሉ። እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።
5በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል። ይሁዳም በደቡብ ድንበር ባሉበት ይጸናሉ፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀጥላሉ።
6እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ትጽፋላችሁ፥ የጻፋችሁትንም ወደ እኔ ታመጣላችሁ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
7ለሌዋውያንም ርስት የላቸውም፤ የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና። የጋድም፥ የሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀበሉ።ይህም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸው ርስታቸው ይህ ነው።
8ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ ሂዱ፥ በምድሩም ላይና ታች ዞራችሁ ጻፉት፥ ከዚያም ወደ እኔ ተመለሱ። በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
9ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ላይና ታች ዞሩ። እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ ዝርዝራቸውንም ጻፉት። ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።
10ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጠላቸው። በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን አካፈላቸው።
11የምድሩም ዕጣ ለብንያምም ነገድ በየወገኖቻቸው ተሰጠ። የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ነበረ።
12በሰሜን በኩል ድንብራቸው ከዮርዳኖስ ይጀራል። ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን በኩል፥በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ደረሰ። መውጫውም በቤት አዌን ምድረ በዳ ነብረ።
13ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ። ድንበሩም በታችኛው ቤት ሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮት አዳር ወረደ።
14ድንበሩም ወደ ምዕራብ ዘለቀ፥ በቤⶆሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ይዞራል፤ መውጫውም ቂርታትይዓሪም በትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያት በኣል ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።
15የደቡብም ዳርቻ ከቂርያት ይዓሪም ውጪ ይጀምራል። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ሄደ።
16ድንበሩም በበን ሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰንን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይን ሮጌልም ወረደ።
17ወደ ሰሜንም ዞረ፤ በኢን ሳሚስ አቅጣጫ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎትወጣ፤ ከዚያሜ ወደ ሮቤ ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤
18በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ።
19ድንበሩም ወደ ቤት ሖግላ ወደ ሰሜን በኩል አለፈ። መውጫውም በዮርዳንስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበር፥ ይህም የደቡቡ ዳርቻ ነበረ።
20በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙሪያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ።
21የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻችቸው እነዚህ ነበሩ፦ ኢያሪኮ፥ ቤት ሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥
22ቤት ዓረባ፥ ዘማራይም፥ ቤቴል፥
23ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥
24ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፣ ጋባ፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
25ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥
26ምጽጳ፥ ከፊራ፥አሞቂ፥
27ፍርቄም፥ይርጵኤል፥ ተርአላ፥
28ዼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባልየኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት፤ አሥራ ሦስት ከትሞችና መንደሮቸችው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።