መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 17

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለምናሴ ነገድ የተመደበው ይህ ነበር፤ እርሱም የዮሴፍ በኩር ነበር። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ራሱም የገለዓድ አባት ነበር። የማኪርም ወገኖች የገለዓድና የባሳን ምድር ተሰጣቸው ምክንያቱም ማኪር የጦር ሰው ነበርና።
2ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው ለአቢዔዝር ልጆች፥ለኬሴግ ልጆች ለአሥሪኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለአፌር ልጆች፥ልሸሚዳ ልጆች ተሰጣቸው። የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ወንዶች ልጆች በየወገኖቻቸው የተሰጣቸው እነዚህ ናቸው።
3ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፤ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩአቸውም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።
4እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርም ሙሴን ከወንድሞቻችን ጋር ርስት እንዲሰጠን አዝዞ ነበር። ስለዚህ ትእዛዙን በመከተል በአባታቸው ወንድሞች መካከል ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው።
5በዮርዳኖስ ማዶ ካለው በገለዓድና በባሳን ምድር ለምናሴ አሥር የመሬት መደቦች ተመድቦ ነበር፤
6ምክንያቱም የምናሴ ሴቶች ልጆች ከወንዶቹ ጋር ርስት ተቀብለዋል። የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ነገድ ተመደበ።
7የምናሴም የድንበር ክልል ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ደረሰ። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ታጱዋ ምንጭ አጠገብ ወደሚኖሩ ሰዎች አለፈ።
8(የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ከተማ ግን ለኤፍሬም ነገድ ሆነ።)
9ድንበሩም ወደ ቃና በኩል ወደ ታች ወረደ። እነዚህ ከወንዙ በስተደቡብ ያሉ ከተሞች በምናሴም ከተሞች መካከል ለኤፍሬም ሆኑ። የምናሴም ድንበር በወንዙ በስተሰሜን በኩል ሆኖ በባሕሩ መጨራሻ ነበረ።
10በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ የነበረው ድንበሩ ባሕር ነበረ። በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅ ም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ።
11በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤት ሳንና መንደሮችዋን፥ ይብልዓምንና መንደሮችዋን፥ ዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የዓይንዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን፥ የታዕናክ ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የመጊዶ ሰዎችንና መደሮችዋን ፥ ሦስቱ ኮረብቶች ምናሴ ወረሳቸው።
12ሆኖም የምናሴ ነገድ ግን እነዚህን ከተሞች ርስት አድርጎ ሊወስዳቸው አልቻሉም፤ ምክንያቱም ከነዓናውያን በዚያ ምድር መኖራቸውን ቀጥለው ነበር።
13የእስራኤልም ሕዝብ እየጠነከሩ በመጡ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከምካከላቸው እንዲወጡ አላደረጉም ነበር።
14ከዚያም የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ እኛ ብዙ ሕዝብ ሆነን ሳለን፥ እግዚአብሔርም ባርኮን እያለ ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን? አሉት።
15ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ በቁጥር ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ወደ ዱር ወጥታችሁ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለራሳችሁ መንጥሩ። ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦአችሁ እንደ ሆነ ይህንን አድርጉ።
16የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉ፦ '"ተራራማውም አገር አይበቃንም። ነገር ግን በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤት ሳንና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰርገሎች አላቸው።"
17ከዚያም ኢያሱ ለዮሴፍ ልጆች መለሰላቸው፦ ለመሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፥ ጽኑም ኃይልም አላችሁ። አንድ ክፍል መሬት ብቻ ሊኖራችሁ አይገባም።
18ተራራማውም አገር ለእናንተ ይሆናል። ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩአቸዋላችሁ፥ ለእናንተም እንዲሆኑ ታደርጋላችሁ። ከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ያሉአቸውና ኃይለኞች ቢሆኑም ልታስለቅቁአቸው ትችላላችሁ። ታሳድዳቸዋላችሁ አላቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።