መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 16

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የዮሴፍም ልጆች የመሬት ድልድል በኢያሪኮ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል ወጣ።
2ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ።
3ወደ ምዕራብም እስከ የፍርሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤት ሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ዘልቆ፥ መጨራሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበር።
4የዮሴፍም ነገድ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን የተቀበሉት በዚህ መንገድ ነበር።
5የኤፍሬምም ነገድ ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፦ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮት አዳር እስከ ላይኛው ቤት ሖሮን ድረስ ነበረ፤
6ከዚያ ወደ ባሕሩ ቀጠለ። ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ ሚክምታት በሰሜን በኩል ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናት ሴሎ ዞረ፥ ከዚያም ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ።
7ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ።
8ድንበሩም ካታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። የኤፍሬም ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ፤
9ይኸውም፥ በምናሴ ነገድ ርስት መካከል ለኤፍሬምም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው።
10በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም ነበር፤እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ሆኖም እነዚህ ሰዎች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ተደርገው ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።