መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው መሬትን ማከፋፈል እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብም መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው።
2በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕረ ልሳን ነበረ።
3ከዚያም ቀጥሎ ከኮረብታ በስተደቡብ በኩል ወደ ጺንም አለፈ፤በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይዘልቃል፤ በሐጽሮንም በኩል አልፎ ወደ አዳርም ደረሰ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥
4ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንባሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበር፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።
5በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዩርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበር።
6ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሖግላ ወጣ፥ በቤት ዓርባ በሰሜን በኩል አለፈ። (ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን) ድንጋይ ወጣ።
7ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ኮረብታ ፊት ለፊት፥በወንዙም በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ዞረ። ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይን ሮጌል አጠገብ ነበረ።
8ከዚያ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ (ኢየሩሳሌም) ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ።
9ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ። ቂርያትይዓሪም ወደምትበል ወደ በኣላ ደረሰ። (ከዚያም ድንበሩ በባኣላ ዙሪያ እንደ ቂርያት በተመሳሳይ ታጠፈ) ።
10ድንበሩም ከባአላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረድ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
11ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ወደ ሽክሮን ደረሰ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
12በምዕራቡም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ።ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
13እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት አርበቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም ዘርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።
14ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴስን፥ አኪመንንና ተላሚን ከዚያ አሳደደ።
15ከዚምም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያት ሤፍር ትባል ነበር።
16ካሌብም እንዲህ አለ፦ ቂርያት ሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ።
17የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት። ስለዚህም ካሌብ ልጁን ዓክሳን አጋባው።
18ዓክሳም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ ለመለምን ገፋፈችው፤ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፤ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት።
19እርስዋም፦ ስጦታ ስጠኝ፤ የኔጌቭ ምድር ሰጥተኸኛል፥ አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
20በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ የተሰጠ ርስት ይህ ነው።
21በድቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉትን የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ ቀብስኤል፥ ዓዴር፥ ያጉር፥
22ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥
23ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን
24ዚፍ፥ጠሌም፥በዓሎት።
25ሐጾርሐ ዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርታይሐጾር፥
26አማም ሽማዕ፥ ሞላዳ፥
27ሐጸርጋዳ፥ሐሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥
28ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥
29በኣላ፥ ዒዮም፥ ዓጼም፥
30ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥
31ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥
32ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞም፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
33በቆላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥
34ዛኖዋ፥ ጫይንገኒም፥ ያጱዋ፥ ዓይናም፥
35የሩት፥ ዓዶላም፥ ሰኮት፥ ዓዜቃ፥
36ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግርራ፥ ግርሮታይም፤ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
37ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥
38ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥
39ለኪሶ፥ በጽቃት፥ አግሎን
40አዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥
41ግዴሮት፥ ቤት ዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤አሥራ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
42ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥
43ይፍታሕ፥ አሽና፥ንጺብ፥
44ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
45አቃሮን፥ ከተመሸጉና ካልተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ ጋር፤
46ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር።
47በአዛጦን የተመሸጉና መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ካርቻ ክረስ።
48በተራራማውም አገር ሳምር፥ የቲር፥ ሶኮ፥
49ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥
50ዓባብ፥ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥
51ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ አሥራ አንድ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
52አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥
53ያንም፥ ቤትታጱዋ፥ አፌቃ፥
54ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
55ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣም
56ኢይዝራሴል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥
57ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ አሥር ከተሞና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
58ሐልሑል፥ ቤት ጹር፥ ጌዶር፥
59ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፤ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
60ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያት በኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
61በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥
62ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
63በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።