መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤልም ሕዝብ በካነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ በእስራኤልም ነገድ መካከል የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤
2እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገዶችና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አካፈሉአቸው፤
3ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።
4የዮሴፍ ነገድ፥ ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ። ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተወሰኑ ከተሞች፥ ለእንስሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
5እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ሕዝብ አደረጉ፥ ምድሩንም ተካፈሉ።
6የይሁዳም ነገድ በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ። ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ።
7የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቤ እንደ ነበረ መረጃ አመጠሁለት።
8ነገር ግን ከእኔ ጋር የሄዱ ወንድሞቼ የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ። እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ።
9ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ።
10አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገር በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲጓዙ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ። እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።
11ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበር፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት፥ ለመውጣትና ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።
12እንግዲህ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ። አንተም በዚያ ቀን ታላላቅና በተመሸጉ ከተሞቻቸው ጋር ዔናቃውያን በዚያ እንደ ነበሩ ሰምተህ ነበር። እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይሆናል፥ አሳድዳቸዋለሁ።
13ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው።
14ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆንች።
15የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር። (አርባቅም በዔናቅ ሰዎች መካከል ከፍ ያለ ነበረ።) ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።