መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፤ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርቶአል።
2የቀረውም ምድር ይህ ነው፤ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥
3(በግብፅ ፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል አስካለው የከነዓናውያን ንብረት ሆኖ ተቆጠረው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን የአስቀሎና፥የጌትና የአቃሮን አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት።)
4በደቡብም በኩል የከነዓናውያንም ምድር ሁሉ፥ ለሲዶናውያንም የምትሆን መዓራ እስከ አሞራውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥
5የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ሊባኖስ ሁሉ፥ ከኣል ጋድ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሐማት ድረስ ያለው ።
6በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ። እነዚህን ከእስራኤል ፊት አባርራቸዋለሁ። እንዳዘዝሁም፤ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ ለመመደብ እርግጠኛ ሁን።
7አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል።
8የእግዚእብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከሌላ እኩሌታ የምናሴ ነገድ ጋር የሮብልና የጋድ ሰዎች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ አዞአቸው የነበረውን ርስታቸውን ተቀበሉ።
9በአርኖን ወንዝ ሸለቆ ዳር ካለው ከአሮዔር፥ (በሸለቆውም መካከል ካለው ከተማ ጀምሮ) የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥
10በሐሴቦንም የአሞርውያን ንጉሥ የሴዎን ከተሞች ሁሉ እስከ አሞራውያን ዳርቻ ድረስ፥
11ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንና የማዕካታውያንን አካባቢ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥
12በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እነርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።
13ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ጌሹራውያንን ወይም ማዕካታውያንን አላወጡም ነበር። በዚህ ፈንታ ጌሹርና ማዕካት እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።
14ሙሴም ለሌዊ ነገድ ለብቻ ርስት አልሰጠም። እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የሚቀረበው፥ በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው።
15ሙሴም ለሮቤል ልጆች ነገድ በየወገናቸው ርስትን ሰጥጣቸው።
16ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀሞሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥
17ሐሴቦንና በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ዲቦን፥ ባሞት በኣል፥ ቤት በኣልምዖን፥
18ያሀጽና ቅዴሞት፥ ሜፍዓት፥
19ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ ጼሬትሻሐና በሸለቆውም ተራራ ያለውና ሁሉ ሮቢን ተቀበለ።
20ሮቤም ቤተ ፌጎርን፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድርን፥ ቤት የሺሞትን፥
21የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት፥ በሐሴቦንም የነገሠው፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የምድያምን አለቆች፥ ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርንና ሪባን፥ የሴዎን መሳፍንት፥ መታቸው።
22የእስራኤል ሰዎች ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ።
23የሮቤል ነገድ ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝ ነው፥ ይህም ድንበራቸው ነው። ይህም ከከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው በየወገኖቻቸው ለሮቤል ነገድ የተሰጣቸው ርስት ነበረ።
24ይህም መሴ ለጋድ ነገድ በየውገኖቻቸው ርስት አድርጎ የሰጣቸው ነው።
25ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያንም ምድር እኩሌታ፥
26ከረባት በስተምሥራቅ፥ አስካለው እስከ አሮዔር ድረስ፥ ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ ነበር።
27ሙሴም ቤትሀራምን፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን፥ የቀሩትንም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ከዮርዳኖስን እንደ ድንበር በምሥራቅ በኩል ባለው በዩርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ሰጣቸው።
28ይህም የጋድ ነገድ ከከተሞቻቸውና ከመንደሮቻቸው ጋር በየወገኖቻቸው ርስት ነበረ።
29ሙሴም ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ርስትን ሰጣቸው። ለምናሴም ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው መሠረት የተመመደበ ነበረ።
30ድንበራቸውም ባሳን ሁሉ፥ ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ በባሳንም ያሉት የኢያፅር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፤
31የገለዓድም እኩሌታ፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበር፤ (የ'ዐግ በባሳን ያሉ የመንግሥት ከተሞች) ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለማኪር ሰዎች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
32ይህም ሙሴ በምሥራቅ በኩል በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሳለ፥ የከፈለው ርስት ነው።
33ሙሴም ለሌዊ ነገድ ርስት አልሰጣም ነበር። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ርስታቸው ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።