መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤልም ሰዎች ድል ያደረጉአቸው ነገሥታት እነዚህ ነበሩ። እስራኤላውያንም ከአዮርዳኖንም ሸለቆ በስተ ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ፥ ከአርሞን ወንዝ ሸለቆ ወደ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ። የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን በሐሴቦን ተቀመጠ።
2በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ገዛ።
3ሴዎንም በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓርባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥በቤት የሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር (እስከ ጨው ባሕር) ወደ ምሥራቅ ድረስ በደቡብም በኩል ከፍስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ገዛ።
4የባሳን ንጉሥ ዐግ ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀመጠ።
5እርሱም የአርሞንዔምንም ተራራ፥ ስልካንና ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ፥ እስከ ንጉሥ ሀሴቦን ድረስ ገዛው ።
6የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፤ ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
7ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ያሸነፉአቸ ነገሥታትና አገሮች እነዚህ ናቸው፡- በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል፥ በሊባኖስ ሸለቆ አጠገብ ወደ ኤዶን አጠገብ ሃላክ ተራራ ድረስ ነው። ኢያሱም ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ ምድሪቱን ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
8ተራራማውን አገር፥ በቆላውንም፥ በዓረባንም፥ የተራሮችን ቁልቁለት፥ ምድረ በዳውንም፥ የደቡቡም ያሉትን ኬጢያውያን፥ አሞራውያንም፥ ከነዓናውያንም፥ ፌርዛውያንም፥ ኤዊያውያንም፥ ኢያቡሳውያንም ሰጣቸው።
9የኢያሪኮ ንጉሥ ጨምሮ፦ በቤቴል አጠገብ ያለው የጋይ ንጉሥ፥
10የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥
11የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥
12የአግሎን ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥
13የዳቤር ንጉሥ፥ የጌድር ንጉሥ፥
14የሔርማ ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥
15የልብና ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥
16የመቄዳ ንጉሥ፥ የቤቴል ንጉሥ፥
17የታጱዋ ንጉሥ፥ ይአፌር ንጉሥ፥
18የአፌቅ ንጉሥ፥ የሽሮን ንጉሥ፥
19የማዶ ንንጉሥ፥የአሶር ንጉሥ፥
20የሺምሮን፥ ሚሮን ንጉሥ፥ የአዚፍ ንጉሥ፥
21የታዕናክ ንጉሥ፥የመጊዶ ንጉሥ፥
22የቃዴስ ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዮቅንዕም ንጉሥ፥
23በዶር ኮረብታ የነበረ የዶር ንጉሥ፥ የጌልገላ አሕዛብ ንጉሥ፥
24የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።