መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የአሦርም ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዮባብ ንጉሥ፥ ወደ ማዶን ንጉሥ፥ ወደ ሺምሮን ንጉሥና ወደ አዚፍ ንጉሥ መልእክት ላከ።
2ደግሞም በሰሜናዊ በተራራማው አገር፥ በየርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ከኪኔሬት በስተ ደቡብ ፥ በምዕራቡ ቆላማ አገሮችና ከኮር ኮረብታማ በስተ ምዕራብ ወዳሉት ነገሥታት ላከ።
3በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያንና በኮረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ።
4እንዚህም ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በቁጥርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ከብዙ ወታደሮች ጋር መጡ። ታላቅም ቁጥር ፈረሶችና ሠረገሎች ነበሩአቸው።
5እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኃይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በተቀጠረው ጊዜ ሰፈሩ።
6እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቆርጣለህ፥ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ።
7ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ መጡ። በድንገትም ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ጠላቶቻቸውን አጠቁኣቸው።
8እግዚአብሔርም ጠላትን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። በሰይፍም ስለት አጠቁአቸው፥ ወደ ሲዶና፥ወደ ማስሮን፥ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ በስተምሥራቅ አሳደዷቸው። ከእነርሱም በሕይወት አንድንም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው።
9ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእነርሱ ላይ አደረጉ። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቆረጠ፥ ሠረገሎቻቸውንም አቃጠለ።
10በዚያን ጊዜም ኢያሱ ወደ ኋላ ተመልሶ አጾርን ያዘ። ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለው። (አጾርም የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይነት ነበራች።)
11በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ በሕይወት ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ። አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።
12ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውን ሁሉ ማረካቸው፥ በሰይፍም ስለት አጠፋቸው። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው በሰይፍ ስለት አጠፋቸው።
13እስራኤልም በተራራው ላይ ከተሠሩ ከተሞች ከአጾር በስተቀር ሌሎችን አላቃጠሉም። ኢያሱ ይህችን ለብቻዋ አቃጠላት።
14እስራኤላውያንም ምርኮውን በሙሉ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ። ሕዝቡን በሙሉ ሁሉም ሙት እስኪሆኑ ድረስ በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው። በሕይወት ካለው ፍጡር አንድም አልቀሩም።
15እግዚአብሔር አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው። ኢያሱም እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም።
16ኢያሱም ማለት ተራራማውን አገር፥ ኔጌቭን ሁሉ፥ የጎሶምን ምድር በሙሉ፥ የኮረብታ ግርጌ። የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ፥ የእስራኤልም ኮረብታማ አገርና ቆላማውን የምዕራቡን ቆላዎችን ሁሉ፥ያንን ምድር በሙሉ ወሰደ።
17እንዲሁም እስከ ሴይር በሚደርሰው ከሐላቅ ተራራ አንሥቶ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በዓል ጋድ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውንም ሁሉ ያዘ፥ መትቶም ገደላቸው።
18ኢያሱ ከእነዚህ ነገሥታት ጋር ረጅም ጊዜ ጦርነት አደረገ።
19በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም። እስራኤል ሁሉንም ከተሞች የያዙት በጦርነት ነበር።
20እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ያለ አንዳች ርኅራኄ ፈጽሞ ይደመስሳቸው ዘንድ እስራኤልን እንዲወጉ ልባቸውን ያደነደናቸው ራሱ እግዚአብሔር ነበር።
21በዚያንም ጊዜ ኢያሱ መጥቶ ዔናቅን አጠፋ። ይህንንም በተራራማው አገር በኬብሮን፥ በዳቤርና በአናብ እንዲሁም በመላው ይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን ላይ አደረገ። እርሱም እነርሱንና ከተሞቻቸውን በሙሉ አጠፋቸው።
22ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፥ በጌትና በአሽዶድ ከቀሩት በስተቀር በእስራኤል አገር ከዓናቅ የቀሩት አልነበሩም።
23ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ምድሪቱን በሙሉ ያዘ። ኢያሱም እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራእላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።