መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዮናስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፤
2«ተነሥተህ ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የምነግርህንም መልእክት ስበክላት፡፡»
3ስለዚህም ዮናስ ለያህዌ ቃል በመታዘዝ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷን ዳር እስከ ዳር ለማዳረስ ሦስት ቀን ይወስድ ነበር፡፡
4ዮናስ ወደ ከተማዋ ገባ፤ ከአንድ ቀን ጉዞ በኃላ፣ «ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች» ብሎ ዐወጀ፡፡
5የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፡፡ ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ ሁሉም ማቅ ለበሱ፡፡
6ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱን አወለቀ፣ ማቅም ለብሶ ዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡
7ከዚያም እንዲህ የሚል ዐዋጅ በነነዌ አስነገረ፤ «በንጉሡና በመኳንንቱ» ሥልጣን ከነነዌ የወጣ ዐዋጅ፤ ሰውም ሆነ እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ ምጋ ምንም ነገር አይቅመስ አይብላ ውሃም አይጣጣ፡፡
8ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጮኽ፡፡ ሰው ሁሉ ከክፉ መንገዱ ይመለስ፤ ግፍ መሥራቱንም ይተው፡፡
9እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?»
10እግዚአብሔርም ያደረጉትን፣ ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውንም አየ፡፡ በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት አላመጣም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።