መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዮናስ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ዮናስ ዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ያህዌ ጸለየ፡፡
2እንዲህ አለ፤ «ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ያህዌ ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ እርሱ እንዲረዳኝ ከጥልቁ መቃብር ጮኽኩ አንተም ጩኸቴን ሰማህ፡፡
3ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕሩ መሠረት ጣልኸኝ፤ ፈሳሾች ዙሪያዬን ከበቡኝ፣ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላየ አለፈ፡፡
4እኔም፣ ከፊትህ ጠፋሁ፤ ሆኖም፣ እንደ ገና ወደ ቅዱስ መቅደስህ እመለከታለሁ» አልሁ፡፡
5ሕይወቴን ለማጥፋት ውሆች ሸፈኑኝ፤ ጥልቁም በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕር ዐረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ፡፡
6ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ሕይወቴን ከጥልቁ አወጣህ!
7ነፍሴ በዛለች ጊዜ ያህዌን አሰብሁት፤ ጸሎቴ ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣ፤፤
8ልባቸውን ከንቱ አማልከት ላይ የሚያደርጉ ለእነርሱ ያለህን ጸጋ ያጣሉ፡፡
9እኔ ግን፣ በምስጋና መዝሙር መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈጽማለሁ፡፡ ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው፡፡
10ከዚም ያህዌ ዓሣውን አዘዘ ዮናስንም ደረቁ ምድር ላይ ተፋው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።