መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዮናስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ይህ ግን ዮናስን ደስ ስላላሰኘው በጣም ተቆጣ፡፡
2እንዲህ በማለትም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ «ያህዌ ሆይ፣ ገና በአገሬ ሳለሁ ያልሁት ይህንኑ አልነበረምን? አንተ ቸርና ርኅሩኅ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየህ ምህረትህም የበዛ፣ ጥፋትን ከማምጣት የምትመለስ አምላክ መሆንህን ስለማውቅ ወደ ተርሴስ ለመኮብለል የሞከርኩት በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡
3አሁንም ያህዌ ሆይ፣ ሕይወቴን እንድትወስድ እለምንሃለሁ፣ በሕይወት ከመኖር መሞት ይሻለኛል» አለ፡፡
4ያህዌ ግን፣ «መቆጣትህ ተገቢ ነውን?» አለው፡፡
5ከዚያም ዮናስ ከከተማዋ ወጥቶ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፡፡ በዚያም ለራሱ ዳስ ሠርቶ በከተማዋ የሚደርሰውን ለማየት ከጥላው ሥር ተቀመጠ፡፡
6ያህዌ አምላክም አንድ ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲሆንና ትኩሳቱም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፤ ዮናስም ስለ ተክሉ በጣም ደስ አለው፡፡
7ነገር ግን በሚቀጥለው ጠዋት ፀሐይ ስትወጣ አንድ ትል አዘጋጅቶ ያንን ተክል እንዲያጠቃ አደረገ፤ ተክሉም ጠወለገ፡፡
8ፀሐይ ስትወጣ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፡፡ ፀሐዩ የዮናስንም ራስ አቃጠለ እርሱም ተዝለፈለፈ፡፡ ያኔ ዮናስ መሞት ፈልጐ፣ «ከመኖር መሞት ይሻለኛል» አለ፡፡
9እግዚአብሔርም ዮናስን፣ «ስለ ተክሉ መቆጣትህ ተገቢ ነውን?» አለው፡፡ ዮናስም፣ «አዎን፣ እንዲያውም እስከ ሞት ድረስ መቆጣት ይገባኛል» አለ፡፡
10ያህዌ እንዲህ አለ፣ «አንተ እንዲበቅል ወይም እንዲያድግ ላልደከምህበት ተክል ይህን ያህል አዝነሃል፤ በአንድ ሌሊት በቀለ፤ በአንድ ሌሊትም ደረቀ፡፡
11ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሰዎችና እንስሶች ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን የለብኝምን? ፡፡»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።