መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዮናስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤
2«ተነሣና ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፏቷ ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርሷ ላይ ስበክ፡፡»
3ዮናስ ግን ከያህዌ ፊት ኮበለለ፤ ወደ ተርሴስ ለመሄድም ተነሣ፡፡ ወደ ኢዮጴ ወረደ፡፡ ወደ ተርሴስ በምትሄድ መርከብ ተሳፈረ፡፡
4ያህዌ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስ ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቧን አናወጠ፤ ወዲያውኑ የምትሰበር መስሎ ታየ፡፡
5መርከበኞቹ በጣም ፈሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ ፡፡ የመርከቧ ክብደት እንዲቀልል በውስጧ የነበረው ሸክም ወደ ባሕሩ ተጣለ፡፡ ዮናስ ግን ወደ መርከቧ ታችኛ ክፍል ሄዶ ተኛ፤ ከባድ እንቅልፍ ላይም ነበር፡፡
6የመርከቧ አዛዥ ወደ እርሱ መጥቶ፣ «እንዴት ትተኛለህ? ተነሥና አምላክህን ጥራ! ምናልባትም አምላክህ ያስበንና ከጥፋት ያድነን ይሆናል፡፡ አለው፡፡
7እርስ በርሳቸውም፣ ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ኃጢአት መሆኑን እንድናውቅ ኑ፣ ዕጣ እንጣጣል» ተባባሉ፡፡ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ፡፡
8ከዚያም ዮናስን፣ «ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ምክንያት እንደ ሆነ እባክህ ንገረን፡፡ ሥራህ ምንድነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?» አሉት፡፡
9ዮናስም፣ «እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና ደረቁን ምድር የፈጠረውን የሰማይን አምላክ ያህዌን አመልካለሁ» አላቸው፡፡
10እርሱ ራሱ ነግሮአቸው ስለ ነበር ከያህዌ ፊት እየኮበለለ እንደ ነበር አወቁ፤ ስለዚህ የበለጠ ፈርተው፣ «ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህ ነው?» አሉ፡፡
11ባሕሩ ይበልጥ እየተናወጠ በመሄዱ፣ ሰዎቹ ዮናስን፣ «ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን አንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?» አሉት፡፡
12ዮናስም፣ «አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ያኔ ባሕሩ ጸጥ ይልላችኃል፤ ይህ ታላቅ ማዕበል የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ» አላቸው፡፡
13ሰዎቹ ግን ወደ መሬት ለመመለስ የሚቻላቸውን ያህል ቀዘፉ፤ ይሁን እንጂ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ጀመረ፡፡
14ስለዚህም፣ «ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት እንዳታጠፋን እንለምንሃለን፤ የዚህ ሰው ሞት እኛ ላይ አይሁንብን፤ ምክንያቱም አንተ ያህዌ የወደድኸውን አድርገሃል» በማለት ወደ ያህዌ ጮኹ፡፡
15ዮናስንም አንሥተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡ ቆመ፡፡
16ሰዎቹም ያህዌን እጅግ ፈሩ፡፡ ለያህዌ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለእርሱም ስእለትን ተሳሉ፡፡
17እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ዓሣው ሆድ ውስጥ ኖረ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።