መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ኢዩኤል 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በጽዮን መለከት ንፉ፥ በቅዱስ ተራራዬም ላይ የማስጠንቀቂያ ድምጽ አሰሙ! የእግዚአብሔር ቀን መጥቷልና፥በእርግጥም ቅርብ ነውና፤የም ድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ በፍርሃት ይንቀጥቀጡ።
2እርሱም የጨለማና የጭጋግ ቀን፥የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። ንጋት በተራሮች ላይ እንደሚዘረጋ፥ታላቅና ኃያል ሠራዊት እየመጣ ነው። እርሱን የመሰለ ሠራዊት ከቶ አልነበረም፥ከብዙ ትውልድ በኋላ እንኳን ዳግመኛ አይኖርም።
3በስተፊቱ እሳት ሁሉን ነገር ይበላል፥በስተኋላውም ነበልባል ይንቦገቦጋል። በስተፊቱ ምድሪቱ የዔደን ገነትን ትመስላለች፥በስተኋላው የሚገኘ ው ግን ባዶ ምድረ በዳ ነው።በእርግጥ፥ምንም ከእርሱ አያመልጥም።
4የሠራዊቱ ገጽታ እንደ ፈረስ ነው፥እንደ ፈረሰኛም ይሮጣሉ።
5በተራሮች ራስ ላይ እንደሚሄድ የሰረገላ ድምጽ፥ገለባውን እንደሚበላ የእሳት ነበለባል ድምጽ እያሰሙ፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኃያል ሠራዊት ያኮበኩባሉ።
6በፊታቸው ሰዎች ይታወካሉ፥የሁሉም ፊት ይገረጣል።
7እንደ ብርቱ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፥እንደ ወታደሮችም በቅጥሩ ላይ ይዘላሉ፤እያን ዳንዱ እርምጃውን ጠብቆ ፥ሰልፋቸውንም ሳያፈርሱ፤ ይተማሉ።
8እያንዳንዱ መንገዱን ይሄዳል፥እርስ በእርሳቸው ሳይገፋፉ ይተማሉ፤ምሽጎችን ሰብረው ያልፋሉ፥ነገር ግን ከመስመራቸው አይወጡም።
9ከተማን በድንገት ያጠቃሉ፥በቅጥር ላይ ይሮጣሉ፥ቤቶች ላይ ይወጣሉ፥እንደ ሌቦችም በመስኮቶች ያልፋሉ።
10ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፥ሰማያትም ይናወጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ከዋክብትም ማብራታችውን ያቆማሉ።
11ተዋጊዎቹ እጅግ ብዙ ናቸውና፥ትእዛዙን የሚፈጽሙ ኃያላን ናቸውና፤ እግዚአብሔር በሠራዊቱ ፊት ድምጽን ያሰማል። የእግዚአብሔር ቀን ታላቅና የሚያስፈራ ነውና፤ ማን ሊቆም ይችላል?
12«አሁንም እንኳን» ይላል እግዚአብሔር፥«በፍጽም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ፤ጹሙ፥አልቅሱ፥እዘኑም።»
13ልብሳችሁን ብቻ ሳይሆን ልባችሁንም ቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። እርሱ ቸርና መሐሪ፥ለቁጣ የዘገየ፥ፍቅሩ የተትረፈረፈ ነውና፤ስቃይ ካለብት ከዚህ ቅጣት መመለስ ይፈልጋል።
14ምናልባት ይመለስና ይራራ እንደሆነ፥ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን የሚሆን በረከት በስተኋላው ያተርፍ እ ንደሆነ ማን ያውቃል?
15በጽዮን መለከት ንፉ፥የተቀደሰ ጾም አውጁ፥ የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ።
16ሕዝቡን ሰብስቡ፥የተቀደሰ ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችን፥ልጆችን፥ የሚጠቡትንም ሕጻናት ሰብስቡ። ሙሽራው ከእልፍኛቸው፥ሙሽራይቱም ከጫጉላ ቤታቸው ይውጡ።
17የእግዚአብሔር አገልጋዮች፥ ካህናቱ፥ በቤት መቅደሱ መግቢያ ደጅና በመሠዊያው መካከል ያልቅሱ። እንዲህም ይበሉ፦«እግዚአብሔር ሆይ ለሕዝብህ ራራ፥አሕዛብ ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለእፍረት አሳልፈህ አትስጥ።በአሕዛብ መካከል አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይበሉ።»
18እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ለሕዝቡም ራራ።
19እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦«እነሆ፥ እህል፥አዲስ ወይንና ዘይት እልክላችኋለሁ። እናንተም በእነርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል ለውርደት አላደርጋችሁም።
20የሰሜንን ጥቃት ፈጻሚዎች ከእናተ አርቃለሁ፥ ወደ ደረቅና ወደ ተተወ ምድር እሰድዳቸዋለሁ። የሠራዊቱ ፊተኛ ጦር ወደ ምሥራቅ ባሕር፥ የሠራዊቱ ኋለኛ ጦር ወደ ምዕራብ ባሕር ይሄዳል። ግማቱ ይውጣል፥ክርፋቱም ይነሳል፤ታላላቅ ነገሮችንም አደርጋለሁ።»
21እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ምድር ሆይ አትፍሪ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሴትም አድርጊ።
22የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳ ማሰማሪያዎች ለምልመዋልና፥ ዛፎች ፍሬያቸውን አፍርተዋልና፥ የበለስ ዛፎችና ወይኖች ሙሉ ፍሬያቸውን ሰጥተዋልና፤አትፍሩ።
23የበልግን ዝናብ እንደሚገባ ይሰጣአችኋልና፥እንደ ቀድሞ ዘመን የበልግ ዝናብንና የፀደይን ዝናብ ያካፋላችኋልና፤ የጽዮን ሰዎች ሆይ፥ደስ ይበላችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ሐሴት አድርጉ።
24አውድማዎቹ በስንዴ ይሞላሉ፥መጥመቂያዎችም አዲስ ወይን ጠጅና ዘይት ያፈስሳሉ።
25በመካከላችሁ የላኩት ታላቁ ሠራዊቴ፥ የአንበጣ መንጋ፥ ትልቁ አንበጣ፥ ፌንጣና አባ ጮጋሬ የበሏቸውን የምርት ዓመታት እመልስላችኋለሁ።
26ተትረፍርፎ ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁም፤ በመካከላችሁም ተዓምራት ያደረገውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውኑ አላመጣም።
27እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንኩ፥ ሌላም እንደሌለ፥ ከእንግዲህም ወዲይ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውን እንደማላመጣ ታውቃላችሁ።
28ከዚያም በኋላ እንደዚህ ይሆናል፡- መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ። ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፥ጎልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ።
29በእነዚያ ወራት በወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ላይም መንፈሴን አፈሳለሁ።
30በሰማያት ድንቆችን፥በምድርም ደም፥እሳትና የጢስ ዓምድ አሳያለሁ።
31ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።
32የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል። እግዚአብሔር እንደ ተናገርው፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያመልጡ ይኖራሉ፤ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኛሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።