መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ኢዩኤል 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
2እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ፤በምድሪቱም የምትኖሩ ሁላችሁ አድምጡ። ይህ፥ከዚህ በፊት በእናንተ ወይም በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ያውቃልን?
3ይህንን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው ይንገሩ፥የእነርሱም ልጆች ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ።
4ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን ትላልቁ አንበጣ በላው፥ከትልቁ አንበጣ የተረፈውን ፌንጣ በላው፥ ከፌንጣ የተረፈውን አባ ጨጓሬ በላው።
5እናንተ ሰካራሞች ተነሡና አልቅሱ! አዲሱ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ዋይ በሉ።
6ቁጥር የሌለው ሕዝብ በምድሬ ላይ መጥቶአልና። ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸው፤የሴት አንበሳም ጥርሶች አሉት።
7የወይን ቦታዬን አስደንጋጭ ስፍ ራ አደረገው፤የበለስ ዛፌን መልምሎ ባዶውን አስቀረ። ቅርፊቱን ላጠው፥ጣለውም፤ቅርንጫፎቹም ነጡ።
8ለልጅነት ባሏ ሞት ማቅ እንደ ለበሰች ድንግል አልቅሱ።
9የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዷል፤የእ አብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።
10እርሻው ጠፍቷል፥ምድሪቱም አለቀሰች። እህሉ ወድሟል፥አዲሱ ወይን ደርቋል፥ዘይቱም ተበላሽቷል።
11እናንተ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ስለ ስንዴዉና ስለ ገብሱ እፈሩ። የእርሻው መከር ጠፍቷልና።
12ወይኑ ጠውልጓል፥የበለስም ዛፎች ደርቀዋል፤የሮማን፥የተምርና የእንኮይ ዛፎች፥የእርሻው ዛፎች ሁሉ ጠውልገዋል። ደስታም ከሰው ልጆች ርቋል።
13የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና፥እናንተ ካህናት ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ! ፥እናንተ የመሠዊያው አገልጋዮች ዋይ በሉ። እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች ኑ ሌሊቱን በሙሉ ማቅ ላይ ተኙ።
14ቅዱስ ጾም አውጁ፥የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችንና በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።
15የእግዚአብሔር ቀን ደርሷልና፥ወዮ ለዚያ ቀን! ከእርሱ ጋር ጥፋት ሁሉን ከሚችል አምላክ ይመጣል።
16ምግብ ከዓይናችን ፊት፥ ደስታና ሐሴት ከአምላካችን ቤት አልተወገደምን?
17ዘሩ በምድር ውስጥ በስብሷል፤እህሉ ደርቋልና ጎተራዎቹ ባዶ ሆነዋል፥ጎታዎቹም ፈርሰዋል።
18እንስሳት ምንኛ ጮኹ! መሰማሪያ የላቸውምና የቀንድ ከብት መንጎች ተሰቃዩ። የበግ መንጎችም ተሰቃዩ።
19እሳቱ የምድረ በዳውን ማሰማሪያ በልቷልና፥ነበልባሉም የጫካውን ዛፎች ሁሉ አቃጥሎአልና፤እግዚአብሔር ሆይ ወደ አንተ እጮሃለሁ።
20ጅረቶች ሁሉ ስለደረ ቁና እሳ ት የምድረ በዳውን ማሰማሪያ ስለ በላው፥የዱር እንስሳት እንኳን ወደ አንተ አለኽልኹ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።