መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ኢዩኤል 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እነሆ፥ በዚያ ወራትና በዚያ ጊዜ፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜ፥
2አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ። በአሕዛብ መካከል ከበተኑአቸው ከሕዝቤና ከርስቴ ከእስራኤል የተነሳ፥ ምድሬን ከመከፋፈላቸው የተነሳ፤ በዚያ እፈር ድባቸዋለሁ።
3በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን በሴተኛ አዳሪ ለወጡ፥ ሴት ልጅንም ለወይን ጠጅ ሸጡ፥ ጠጡም።
4ጢሮስና ሲዶና የፍልስጤምም ክፍለ አገራት ሁሉ፥አሁን በእኔ ላይ መቆጣታችሁ ለምንድ ነው? ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን? ብድራትን ብትመልሱልኝ፥ወዲያው ብድራታችሁን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
5ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፥የከበረውንም ሀብቴን ወደ ቤተ መቅ ደሳችሁ አግዛችኋል።
6ከግዛታቸው ልታርቋቸው፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋል።
7እነሆ እነርሱን የሸጣችሁብትን ሥፍራ እንዲለቁ አደርጋቸዋለሁ፥ ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
8ወንዶችና ሴቶች ልጆ ቻችሁን በይሁዳ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ። እነርሱም በሩቅ ላለ ሕዝብ፥ለሳባ ሰዎች ይሸጡአቸዋል። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
9ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፦ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ኃያላን ሰዎችን አነሣሡ፥ ይቅረቡ፥ ተዋጊዎችም ሁሉ ይውጡ።
10ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁን ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፤ ደካማውም «እኔ ብርቱ ነኝ» ይበል።
11እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ፈጥናችሁ ኑ፥ በአንድነትም ተሰብሰቡ። እግዚአብሔር ሆይ ኃያላን ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ።
12በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ልፈርድ በዚያ እቀመጣለሁና፤ አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ ይምጡ።
13መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ላኩ፥ የወይኑ መጭመቂያ ሞልቶ እየፈሰሰ ነውና ኑ ወይኑን ርገጡ፥ ክፋታቸው በዝቶአልና።
14የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ቀርቦአልና፤ ሁካታ፥ በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ሁካታ አለ።
15ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይከለክላሉ።
16እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ከኢየሩሳሌም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፥ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መጠለያ፥ ለእስራኤልም ሕዝብ መመሸጊያ ይሆናል።
17«ስለዚህ በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምኖር እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ ዳግመኛም ሠራዊት አያልፍባትም።
18በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፥የይሁዳ ጅረቶች ሁሉ ውኃ ያጎርፋሉ፥ ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይመነጫል፥ የሰጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
19በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና፥ በምድራቸው የንጽሐንን ደም አፍስሰዋልና፤ ግብጽ ባድማ፥ ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች።
20ነገር ግን ይሁዳ ለዘላለም ይኖራል፥ኢየሩሳሌምም ከትውልድ ትውልድ ትኖራለች።
21ያልተበቀልኩትን ደማቸውን እበቀላለሁ፤» እግ ዚአብሔር በጽዮን ይኖራል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።