1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦
2“ እንዲህ እንደ ሆነ በእውነት አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?
3ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፥ ከሺህ ነገር አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።
4እግዚአብሔር በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ እርሱን ተዳፍሮ በደኅና የተሳካለት ማን ነው?
5በቍጣው ተራሮችን ሲገለብጣቸው፤ ተራሮችን ሲነቅላልቸው ለማን አስቀድሞ ተናገረ።
6ምድርን ከስፍራዋ ያሚያናውጣት እርሱ፥ ምሰሶዎችዋንም ያንቀጠቅጣቸዋል።
7ይኸው እግዚአብሔር ፀሐይን እንዳትወጣ ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ይከልላቸዋል።
8ሰማያትን በራሱ ይዘረጋል፥ የባሕሩን ማዕበል የሚገዛ በላዩም ይራመዳል።
9ድብና ኦሪዮን የሚባሉትን ኮከቦች፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ስብስቦች ሠርቶአል።
10ይኸው እግዚአብሔር የማይመረመሩ ታላላቅ ነገሮችን፥ በርግጥ የማይቈጠሩ ተአምራቶችን ያደርጋል።
11እነሆ፥ ወደ እኔ ቢመጣ አላየውም፤፤ በአጠገቤም ቢያልፍ አላውቀውም።
12እነሆ አንድን ሰው ነጥቆ ቢወስድ የሚከለክለው ማን ነው? ምን እያደረግህ ነው? የሚለውስ ማን ነው?
13እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ የረዓብ ረዳቶች ከእርሱ በታች ይሰግዳሉ።
14ይልቁንስ መልስ ልመልስለት፥ ከእርሱ ጋርስ ለክርክር ቃልን እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
15ጻድቅ ብሆን ኖሮ እንኳ ልመልስለት አልችልም፤ የምችለው ዳኛዬን ምህረት መለመን ብቻ ነው ።
16ብጠራውና እርሱ ቢመልስልኝ ም ኖሮ፥ ድምጼን ይሰማ እንደ ነበር አላምንም ።
17በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛዋል።
18ትንፋሽ እድወስድ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም፥ ይልቅ በመራራነት አጠገበኝ።
19ስለ ኃይል ከተናገርን እንደ እርሱ ኃያል ማን ነው፤ የፍርትህ ነገር ከተነሳ፦”የሚጠይቀኝ ማን ነው? “ ይላል።
20ጻድቅ ብሆን እንኳ አንደበቴ ይወቅሰኛል፤ ሰበብ ባይገኝብኝ እንኳ ጥፋተኛ ያደርገኛል።
21ያለነቀፋ ብሆንም ከእንግዲህ ለራሴ ግድ የለኝም፤ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
22ልዩነት የለውም፤ እርሱ “ጻድቁንና ሃጥኡን ባንድነት ያጠፋል" የምለው ለዚህ ነው።
23መቅሠፍ በድንገት ቢገድል፥ በንጹሐን ሰዎች ችግር ይስቃል።
24ምድር ለኃጥአን እጅ ታልፋ ተሰጥታለች፤ እግዚአብሔርም የዳኞችዋን ፊት ሸፍኖአል፤ ይህን ያረገው እርሱ ካልሆነ ታድያ ማን ነው?
25ዘመኔ ከመልክተኛ ሰው ሩጫ ይልቅ ይፈጥናል፤ ቀኖቼ፥ መልካምን ሳያዩ ይከንፋሉ።
26የደንገል ጀልባ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደሚነጥቀው ግዳይ እንደሚበርር ፈጣን ናቸው።
27“አቤቱታዬን እረሳለሁ፤ ሐዘንተኛ ፊቴን ትቼ ደስተኛ እሆናለሁ” ብዬ ብል፥
28ንጹሕ አድርገህ እንደማትቆጥረኝ ስላወቅሁ መከራዬን ሁሉ እፈራዋለሁ።
29ጥፋተኛ ሆኜ መቀጣቴ ላይቀር፤ ለምን በከንቱ እደክማለሁ?
30ራሴን በአመዳይ ውሃ ባጥብና እጆቼንም እጅግ ባነጻቸው፥
31የገዛ ልብሴ እስኪጸየፈኝ ድረስ እግዚአብሔር በአዘቅት ውስጥ ይመልሰኛል።
32መልስ እድሰጠው ፥ አብረን ወደ ፍርድ ችሎት እንዳንገባ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።
33እጁን በሁለታችንም ላይ የሚያኖር ፈራጅ፤ በመካከላችንም የሚዳኝ የለም!
34የእርሱን በትሩ ከእኔ ላይ የሚያነሳ፥ ማስደንገጡንም ከኔ የሚያርቅ ሌላ ፈራጅ የለምን?
35በሚገባ በተናገርሁ፥ ባልፈራሁም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ነገሮች እንዲህ ባሉበት አልችልም።