መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
2እስከ መቼ እነዚህን ነገሮች ትናገራለህ? የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ብርቱ ነፋስ ይሆናል?
3በውኑ እግዚአብሔር ፍትህን ያቃውሳልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
4ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥ እርሱም በበደላቸው እጅ አሳልፎ እንደሰጣቸው እናውቃለን።
5ነገር ግን እግዚአብሔርን በትጋት ብትፈልገውና፥ ሁሉንም ለሚችለው አምላክ ልመናህን ብታቀርብ፥
6ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ ስለ አንተ ይቆማል፥ በርግጥ የታመነ መኖሪያ ያደርግልሃል።
7ጅማሬህ ትንሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
8ስለ ቀደመው ዘመን ትውልድ ትጠይቅ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አባቶቻቸውም ከመረመሩና ካገኙት ነገር ለመማር ትጋ፤
9(ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ስለሆነ እኛ ትናንት ተወለድን፤ ምንም አናውቅም) ፤
10እነዚህ የሚነግሩህና የሚያስተምሩህ አይደሉምን? ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
11በውኑ ረግረግ በሌለበት ደንገል ሳር ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
12ገና ለምለም አረንጓዴ ሆኖ ሳይቈረጥ፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይጠወልጋል።
13እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ የመንገዳቸው ፍጻሜ እንዲሁ ነው፤ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋም ይጠፋል።
14መታመኛቸው እንደሚናድባቸው፥ እምነቱም የሸረሪት ድር አይነት የሆነበት።
15እዲህ አይነት ሰው ቤቱን ይደገፋል፥ነገር ግን አይቆምለትም፤ደግፎም ይይዘዋል፥ አይጸናለትም።
16ፀሐይም እንደወጣች ይለመልማል፥ ጫፉም በአትክልቱ ቦታ ጎልቶ ይወጣል።
17ሥሮቹ በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጠማሉ፤ በድንጋዮቹም መካከል መልካም ቦታን ይፈልጋሉ።
18ነገር ግን ይህ ሰው ከቦታው ቢጠፋ፦ ስፍውም "ፈጽሞ አቼህ አላውቅም" ብሎ ይክደዋል።
19እነሆ፥ የደስእንደዚህ አይነትሰው ደስታ ይህ ነው፤ ሌሎች ተክሎች ከዚያው አፈር በፋንታው ይበቅላሉ።
20እነሆ፥ እግዚአብሔር ንጹሁን ሰው አይጥለውም፥ የክፉ አድራጊውንም እጅ አያበረታም።
21አፍህን እንደ ገና ሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በደስታ ጩኊት ይሞላል።
22የሚጠሉህ እፍረትን ይለብሳሉ፤ የአመጸኞችም ድንኳን አይገኝም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።