መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በራሴ ሕይወት ዝያለሁ፤ አቤቱታዬን ያለመቆጠብ እገልጻለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።
2እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ለምን እንደ ከሰስከኝ ንገረኝ እንጂ እንዲያው አትፍረድብኝ።
3የእጅህን ሥራ መናቅ፤እኔንስ ማስጨነቅ የኃጥአንን እቅድ ግን በፈገግታ ስትተወው ይህ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?
4በውኑ አይኖችህ የሥጋ ለባሽ ዓይኖች ናቸውን? ሰውስ እንደሚያይ ታያለህን?
5በደሌን ትከታተል ዘንድ፥ ኃጢአቴንም ትመረምር ዘንድ፥
6ቀኖችህ እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን? ዓመታትህስ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?
7በደለኛ እንዳልሆንሁ ብታውቅም እንኳ፥ ከእጅህ ሊያድነኝ የሚችል የለም።
8እጆቸህ አበጃጁኝ አሳምረህም ሠራኸኝ፤ መልሰህ ግን እያታጠፋኸኝ እኮ ነው።
9እለምንሃለሁ፤ እንደ ሸክላ አበጃጅተህ እንደ ሰራኸኝ አስብ፤ እንደገናስ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
10እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን? እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?
11ስጋን አደረክልኝ ቁርበትንም አለበስኸኝ፥ በአጥንትና በጅማትም አቀናብረህ አጠነከርኸኝ።
12ሕይወትና የታመነ ኪዳን ሰጠኸኝ፤ እርዳታህም መንፈሴን ጠበቀ።
13ነገር ግን እነዚህንም ነገሮች በልብህ ሰወርህ፤ ይህንንም ታስብ እንደነበር አውቃለሁ።
14ኃጢአትም ባደርግ አንተ ታውቀዋለህ፤ ከአመጻዬም ነጻ አትለቀኝም።
15በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ ጻድቅ ብሆንም ራሴን ቀና አላደርግም፤ በሃፍረት ተሞልቼአለሁና፥ መከራዬንም እያየሁ ነውና።
16ራሴንም ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤ እንደገና ሃያል መሆንህን ታሳየኛለህ፤
17አዲስ ምስክሮችህን ታቆምብኛለህ ቍጣህንም በላዬ ታበዛብኛለህ፤ በአዲስ ሰራዊትም ታጠቃኛለህ።
18ታዲያ ለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ምነው ያኔ ነፍሴ በጠፋችና የሰው ዓይን ባላየኝ።
19ኖሮ እንደማያውቅ በሆንሁና፤ ከማኅፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
20የቀሩኝ ቀናቶች ጥቂት አይደሉምን? ታዲያ ጥቂት እንዳርፍ ተወት አድርገኝ፤
21ወደማልመለስበት ከመሄዴ በፊት፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥
22እንደ እኩለ ለሊት ወደ ጨለመች ምድር፥ ሥርዓትም ወደሌለበት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።