መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለእያንዳንዱ ሰው ህይወት በምድር ብርቱ ልፋት አይደለምን?ቀኖቹስ እንደ ተቀጣሪ ሰራተኛ ቀኖች አይደሉምን?
2የምሽት ጥላን እንደሚመኝ አገልጋይ፤ደመወዙንም በጽኑ እንደሚፈልግ ቅጥረኛ፤
3እንዲሁ የጉስቁልና ወራትና፤ መከራ የተሞሉ ለሊቶችን በጽናት እንዳልፍ ተሰጡኝ።
4በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? ሌሊቱስ መቼ ያልፋል እላለሁ። እስኪነጋ ድረስም ወዲያና ወዲህ እገላበጣለሁ።
5ሥጋዬ ትልና የአመድ ቅርፊት ለብሶአል፤ ደርቆ የነበረው የቆዳዬም ቁስል እንደ ገና ያመረቅዛል።
6ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ፈጣን ናቸው፥ ያለ ተስፋም ያልፋሉ።
7ሕይወቴ አንድ ትንፋሽ እንደ ሆነ፤ ዓይኔም መልካም ነገርን ከእንግዲህ አንደማያይ አሳሰበኝ።
8የሚያየኝ የእግዚአብሔር ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ዓይኖችህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔ ግን አልገኝም።
9ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንደዚሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ተመልሶ አይወጣም።
10ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥ የነበረበት ስፍራውም ዳግመኛ አያውቀውም።
11ስለዚህም አፌን አልገድበውም፤ በመንፈሴ ስቃይ ሆኜ እናገራለሁ፤ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አቤቱታዬን አቀርባለሁ።
12ጠባቂ በላዬ ትቀጥርብኝ ዘንድ፥ እኔ ባሕር ወይስ የባህር አውሬ ነኝን?
13እኔም፦ "አልጋዬ ያጽናናኛል፥ መቀመጫዬም የኀዘን እንጕርጕሮዬን ያቀልልኛል" ባልሁ ጊዜ፥
14አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
15ስለዚህም እኔ አጥንቴን ከምታገስ ይልቅ መታነቅንና ሞትን እመርጣለሁ።
16ለዘላለም መኖርን እንዳልመኝ፤ ሕይወቴን ናቅኋት። ቀኖቼ ዋጋ ቢስ ናቸውና እባካችሁ ተዉኝ።
17ትኩረት ትሰጠው ዘንድ ፥ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድር ነው፥
18ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ በየጊዜውስ ትፈትነው ዘንድ?
19የማትተወኝ እስከ መቼ ነው? ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
20ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ ኅጢያትንስ አድርጌ እንደ ሆነ ይህ ላንተ ምንድን ነው? ሸክም እ ሆንብህ ዘንድ? ስለ ምን የኢላማሀ ግብ አደረግኸኝ?
21መተላለፌን ይቅር ብለህ ስለ ምን ጉስቁልናዬን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በጥንቃቄም ትፈልገኛለህ፥ አታገኘኝም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።