መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦
2ኦ ስቃዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!
3ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና ለዚህ ነው ቃሎቼ የድፍረት ቃላት የሆኑት።
4ሁሉን የሚችል አምላክ ቀስት በውስጤ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ በእኔ ላይ ተሰልፎአል።
5በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በዝለት ያናፋልን? በሬስ ገለባ እያለው በረሀብ ይጮኻልን?
6ጣዕም የሌለው ነገርስ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ በእንቁላል ውኃ ውስጥ ጣዕም አለን?
7ለመንካት ሰውነቴ እምቢ አላቸው፤ እንደሚያስጸይፍ ምግብ ሆኑብኝ።
8ምነው ልመናዬ በደረሰልኝ! እግዚአብሔርም መሻቴን ምነው በሰጠኝ!
9እግዚአብሔርም አንድ ጊዜ እኔን ማጥፋት ደስ ቢያሰኘው እጁንም ዘርግቶ ከዚህ ሀይወት ቢያስወግደኝ!
10ይህም መጽናናት ይሆንልኛል፤ በማይበርድ ሕመም ውስጥ ብሆንም፥ የቅዱሱን ቃል አልክድምና።
11እድጠብቅ አቅሜ ምንድን ነው? የምታገሰውስ የህይወቴ ፍጻሜ ምን ስለሆነ ነው?
12ጕልበቴ የድንጋይ ጕልበት ነውን? ወይስ ሥጋዬ የተሰራው ከናስ ነውን?
13በእኔ ውስጥ ሊረዳኝ የሚችልነገር እንደሌለ ጥበብም ከእኔ እንደ ተባረረ እውነት አይደለምን?
14ሁሉን የሚችል አምላክን መፍራት የተወ ሰው፥ በዝለት ሊወድቅ ለቀረበ ስንኳ ታማኝነት ከወዳጁ ሊሆንለት ይገባል።
15ነገር ግን ወንድሞቼ ጥቂት ቆይቶ ውሃ እንደማይኖረው r እንደ በረሃ ወንዝ የማይታመኑ ሆኑብኝ።
16ከበረዶ የተነሣ ፥በውስጡም ከተሰወረው አመዳይ፤ ወንዙ ደፍርሶ ይጠቁራል፥
17ሙቀትበመጣ ጊዜ ይደርቃሉ፤ በበጋም ወቅት ከስፍራቸው ይጠፋሉ።
18ተጔዥ ነጋዴዎች ውሃ ፍለጋ መንገዳቸውን ሲቀይሩ፤ ወደ በረሃ ገብተው ተቅበዝብዘው ይጠፋሉ።
19የቴማን ነጋዴዎች በዚያ ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ አደረጉ።
20ውሃ እንደሚያገኙ ተማምነው ነበርና አፈሩ፤ ወደዚያ ደረሱ፥ ነገር ግን ተታልለው ነበር።
21አሁንም እናንተ እንዲሁ ደረቅ ሆናችሁብኝ መከራዬን አይታችሁ ለራሳችሁ ፈራችሁ።
22በውኑ እኔ፦”አንዳች ነገር ስጡልኝ? ፤ ከሃብታችሁ ስጦታ አቅርቡልኝ?
23ወይስ፦ ከጠላቴ እጅ አድኑኝ? ከአስጨናቂዎቼ እጅ ተቤዡኝ“ ብያችኋለሁን?
24አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምን ጋር እንደተሳሳትሁ አስረዱኝ።
25የእውነት ቃል እንዴት ያማል! ነገር ግን የእናንተ ሙግት እንዴት እኔን ይገሥጻል?
26ተስፋ እንደ ሌለው ሰው ንግግር ቃሌን እንደ ነፋስ ችላ ለማለት ታስባላችሁን?
27በርግጥ አባት አልባ በሆኑ ልጆች ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤ ለወዳጆቻችሁም ጕድጓድ ትቈፍራላችሁ።
28አሁንም፥ እባካችሁ፥ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ በእርግጥ በፊታችሁ አልዋሽም።
29እባካችሁ፥ ተመለሱ፤ ፍትህ አልባነት በእናንተ መካከል አይሁን፤ በርግጥ ምክንያቴ ጽድቅ ነውና መለስ በሉ።
30በውኑ በምላሴ ክፋት አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።