መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 32

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ስላስቀመጠ እነዚያ ሦስቱ ሰዎች ምላሽ መስጠት አለብህ።
2ከራም ቤተሰብ የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እጅግ ተቆጣ፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ስላጸደቀ ኢዮብን ተቈጣው።
3ደግሞም በኢዮብ ፈረዱበት እንጂ የሚገባ መልስ ስላልሰጡት በሦስቱ ጓደኞቹ ላይ ተቈጣ።
4ከእርሱ ይልቅ ሰዎቹ ሽማግሌዎች ስለነበሩ ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር ለመነጋገር ተራውን ይጠብቅ ነበር።
5ቢሆንም ግን ኤሊሁም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ሲያይ በጣም ተቆጣ።
6ቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ መናገር ሲጀምር እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ወጣት ነኝ፥ እናንተም ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ሰጋሁ፤ እውቀቴን እንዳልናገር ራሴን ገታሁ።
7እንደዚህም አልሁ፦ የቀናት ርዝመት ንግግርን፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ሊያስተማሩ ይገባ ነበር።
8ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጠዋል።
9ታላላቅ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ጥበበኞች አይደሉም፣ በእድሜ የገፉ ስለሆኑ ብቻም ፍትሕን አያስተውሉም።
10ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፥ 'አድምጡኝ፤ እኔም ደግሞ የማውቀውን እነግራችኋለሁ'።
11ተመልከቱ፥ እስክትናገሩ ጠበቅኋችሁ፥ ምን መናገር እንዳለባችሁ በማሰብ ላይ እያላችሁም ክርክራችሁን አዳመጥኩኝ።
12በርግጥ ትኩረቴን ሰጠዃችሁ፥ ነገር ግን፥ ተመልከቱ፥ አንዳችሁም ኢዮብን ማስረዳት ወይም ለቃሎቹ ምላሽ መስጠት አልቻላችሁም።
13'ጥበብን አግኝተናል!' እንዳትሉ ተጠንቀቁ ኢዮብን ማሸነፍ ያለበት እግዚአብሔር ነው፤ ተራ ሰው ይህንን ለማድረግ አይችልም።
14ኢዮብ እኔን በመቃወም አልተናገረምና እኔም የእናንተን በሚመስል ቃል አልመልስለትም።
15እነዚህ ሦስት ሰዎች ዲዳ ሆነዋል፤ ከዚህ በኋላ ለኢዮብ ሊመልሱለት አይችሉም፤ ቀጥለው የሚናገሩት አንድም ቃል የላቸውም።
16እዚያ በዝምታ ስለቆሙና ከእንግዲህ ስለማይመልሱ፥ ስለማይናገሩም፥ መጠበቅ አለብኝ?
17አይሆንም፥ እኔም ደግሞ የበኩሌን እመልሳለሁ፤ እኔም ደግሞ ዕውቀቴን እነግራቸዋለሁ። ቃል
18ተሞልቻለሁና፤ በውስጤ ያለው መንፈስም ይገፋፋኛል።
19ተመልከቱ፥ ውስጤ ተከድኖ እንደሚብላላ ወይን ነው፤ ሊፈነዳ እንደተቃረበ አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳም ነው።
20አርፍ ዘንድ እናገራለሁ፤ አፌንም ከፍቼ መልስ እሰጣለሁ።
21አድልዎ አላደርግም፤ የትኛውንም ሰው አላቆላምጥም።
22እንዴት እንደማቆላምጥ አላውቅምና፤ እንዲህ ባደርግ ኖሮ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ያስወግደኝ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።