መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 30

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጎን እንዳይሰሩ ልከለክላቸው የምችል የነበሩ እነዚህ ወጣቶች፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።
2በርግጥ የአባቶቻቸው ክንድ ጥንካሬ ምን ሊፈይድልኝ ይችል ነበር? የጉልምስናቸው ጥንካሬ ጠፍቶባቸው ነበርና።
3በድህነትና በራብ የመነመኑ ናቸው፤ በደረቅ መሬት በምድረ በዳ ጨለማና ጥፋት ይሰቃያሉ።
4ከቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚሉትን ቅጠሎች ይለቅማሉ፤ የክትክታ ሥራሥር ምግባቸው ነበር።
5ሌባን እየተከታተሉ እንደሚጮኹበት፤ ከሚጮኹባቸው ሰዎች ተለይተው ተሰደዱ።
6በወንዝ ሸለቆ በምድር ጕድጓድና በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሩ ነበር።
7በቍጥቋጦ መካከል እንደ አህያ ይጮኻሉ፤ ከቁጥቋጦ በታች በጋራ ተሰብስበዋል።
8በርግጥ የሰነፎችና ዋጋ የሌላቸው ሰዎች ልጆች ናቸው፤ እየተገረፉ ከምድሪቱ ተባረዋል።
9አሁን ግን ለልጆቻቸው የስላቅ ዘፈን ሆንኩላቸው፤ በርግጥም የነሱ መቀለጃ ሆኛለሁ።
10ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ርቀው ይቆማሉ፤ ፊቴም ላይ መትፋትን አያቆሙም።
11እግዚአብሔር የቀስቴን መወጠሪያ አላልቶብኛል፥ መከራም አሳይቶኛል፤ እነርሱም በፊቴ ይሉኝታ የላቸውም።
12በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ ያሳድዱኛል፤ ለእግሬም የጥፋትን ወጥመድ ያደርጋሉ።
13መንገዴን ያበላሻሉ፤ ከልካይ እንደሌላቸው ሰዎች ጥፋትን ገፍተው ያመጡብኛል።
14በሰፊ ፍራሽ ቀዳዳ እንደሚመጣ ሰራዊት ይመጡብኛል፤ በጥፋት ላይ ተንከባልለው መጡብኝ።
15ድንጋጤ በላዬ መጥቶብኛል፥ ክብሬም በነፋስ ያሳደዱት ያክል በነነ፤ ብልጥግናዬም እንደ ደመና ተበተፈ።
16አሁንም ነፍሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ የብዙ ቀናት መከራም ያዘኝ።
17በሌሊት አጥንቶቼ በውስጤ ተወጉ፥ የሚያሰቃየኝ ህመም ፋታ አይሰጠኝም።
18ከእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተያዘ፥ እንደ ቀሚስ መቀነት ተጠቀለለብኝ።
19እርሱ ጭቃ ውስጥ ወረወረኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።
20ወደ አንተ ጮኽሁ እግዚአብሔር፥ አንተም አልመለስህልኝም ቆምሁኝ፥ አልተመለከትኸኝም።
21ተለወጥህብኝ ፤ ጨካኝም ሆንህብኝ፤ በእጅህም ሃይል አሳደድኸኝ።
22በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀምጠኸ ወሰድኸኝም፤ በማእበልም ውስጥ አቀለጥኸኝ።
23ለሕያዋን ሁሉ ወደተወሰነው ቤት፤ ወደ ሞት እንደምትወስደኝ አውቄአለሁ።
24ነገር ግን ሰው ሲወድቅ እጁን እርዳታ ፍለጋ አይዘረጋምን? በችግር ውስጥ ያለ ማንም ለእርዳታ አይጮኽምን?
25በችግር ላለ ሰው አላለቀስሁምን? ለድሆችስ ነፍሴ አላዘነችምን?
26መልካምን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ መጣብኝ፤ ብርሃንን ስጠባበቅ፥ ጨለማ መጣ።
27ልቤ ታወከ፥ እረፍትም አላገኘም የስቃይም ቀናቶች መጡብኝ።
28ያለ ፀሐይ በጨለመ ሰማይ በትካዜ ሄድሁ፤ በጉባኤም መካከል ቆሜ ለእርዳታ እጮኻለሁ።
29ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ጓደኛ ሆንሁ።
30ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከላዬም ተቀርፎ ወደቀ፤ አጥንቶቼም በትኵሳት ተቃጠሉ።
31ስለዚህ በገናዬ ለኀዘን እንጉርጉሮ ፥ እምቢልታዬም ለለቅሶ ጩኸት ተቃኙ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።