መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 27

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ እንዲህም አለ፦
2ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል አምላክን!
3ነፍሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ በአፍንጫዬ እስካለ ድረስ፥
4በርግጥ ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥ ምላሴም ሽንገላን አያወራም።
5እናንተን ትክክል አድርጎ መቀበል ከእኔ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ትክክለኛነቴን በፍጹም አልጥልም።
6ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ እርሱንም አለቅም፤ ከኖርኩባቸው ቀኖቼ ስለ አንዱም ህሊናዬ አይወቅሰኝም።
7ጠላቴ እንደ በደለኛ ሰው ይሁን፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
8እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋው ምንድር ነው?
9መከራ በመጣበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
10ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
11ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፤ የሁሉን ቻይ አምላክን ሃሳብ አልሸሽግም።
12እናንተ ሁላችሁ ይህንን አይታችሁ፤ ለምን ይህን ሁሉ ከንቱ ነገር ተናገራችሁ?
13ይህ እግዚአብሔር ለክፉ ሰው ያቆየው እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ርስት ነው፤
14ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ ዘሩም በቂ እንጀራን አያገኝም።
15የተረፉለትም በመቅሰፍት ምክንያት ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
16አመጸኛ ሰው ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ቢያከማች፥
17እርሱ ያከማቸውን ልብስ፥ ጻድቃን ይለብሱታል፤ ብሩንም ንጹሐን ሰዎች ይከፋፈሉታል።
18ቤቱን እንደ ሸረሪት ይሠራል፥ ጠባቂም እንደሚቀልሰው ጎጆ ይመስላል።
19ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን አይዘልቅበትም፤ ዓይኑን በከፈተ ጊዜ፥ ሃብቱ ሁሉ የለም።
20ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ያገኘዋል፤ ማዕበልም በሌሊት ይወስደዋል።
21የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፥ እርሱም ይለቃል፤ ከስፍራውም ይጠርገዋል።
22ከነፋሱ ሊያመልጥ ይሞክራል፥ ነገርግን ሳያቋርጥ እየተወረወረ ይደርስበታል።
23በመሳለቅም እጁን ያጨበጭብበታል፤ በፉጨትም ከስፍራው ያስወጣዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።