1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2ኃይል የሌለውን እንዴት ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
3ጥበብስ የሌለውን እንዴት መከርኸው! መልካም እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
4እነዚህን ቃሎች በማን እርዳታ ተናገርህ? ስትናገርስ ከአንተ የወጣው መንፈስ የማን ይሆን?
5በልዳዶ ስ መለሰ “ሙታን ሰዎች ከውሃዎች በታች የሚኖሩ፥ጥላዎ ቻቸውም ይንቀጠቀጣሉ።
6ሲኦል በእግዚአብሔር ፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ጥፋትም ቢሆን ራሱን መሸፈኛ የለውም።
7ሰሜንን በባዶ ሕዋ ውስጥ ዘረጋው፥ ምድርንም እንዲያው ባዶ ላይ አንጠለጠላት።
8ውሃዎችን በደመናዎች ውስጥ ያስራል፥ ደመናውም ከታች አልተቀደደችም።
9የጨረቃን ፊት ይጋርዳል፥ ደመናውንም በላይዋ ይዘረጋበታል።
10በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለ መስመር፥ በውሃዎች ላይ ድንበርን አደረገ።
11የሰማይ አዕማድ ተንቀጠቀጡ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ደነገጡ።
12በኃይሉ ባሕርን ጸጥ አደረገ፥ በማስተዋሉም ረዓብን መታ።
13በእስትንፋሱ የሰማያትን ማዕበል ያነጻል፤ ሰማያትም ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች።
14እነዚህም ገና የመንገዱ መጀመሪያ ብቻ ናቸው፤ ከእርሱ የሰማነው ይህ ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉን ነጐድጓድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?