1ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2ገዢነትና መፈራት የእርሱ ናቸው፤ በሰማይ ከፍታውም ስርአትን ያደርጋል።
3በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር ፍጻሜ አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4እንግዲህ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ይሆናል፥ ከሴትስ የተወለደ እንዴት ንጹሕና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል?
5ጨረቃ እንኳ ለእርሱ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
6ይልቁንስ ትል የሆነ ሰው፥ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!