1ቴማናዊውም ኤልፋዝ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2ሰው እግዚአብሔርን መጥቀም ይችላልን? ጥበበኛ ቢሆን እንኳ ይጠቅመዋልን?
3ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን ለሚችለው አምላክ የሚጨምረው ደስታ አለን? መንገድህ ፍጹም ቀና ቢሆን የሚጠቅመው ነገር አለን?
4የሚገስጽህና ወደ ፍርድስ ስፍራ የሚያመጣ፥ እርሱን ስለፈራህ ነውን?
5በደልህ እጅግ የበዛ፣ ኃጢአትህም ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
6ያለምክንያት ከወንድሞችህን መያዣን ወስደሃል፥ ሰዎችን ልብሳቸውን ገፈህ እርቃናቸውን አስቀረሃቸው።
7ለዛሉም ሰዎች ውኃ አልሰጠሃቸውም፥ ከራብተኛ ሰዎችም እንጀራን ከልክለሃል።
8ምድርን የገዛህ ሃያል፤ ክቡር ሰው ብትሆንም።
9መበለቶን ባዶአቸውን ሰድደሃቸዋል አባት የሌላቸው ልጆችም ክንድ ተሰብሮአል።
10ስለዚህ ወጥመድ በዙሪያህ አለ፥ ድንገተኛ ፍርሃት ያናውጥሃል።
11እንዳታይም ጨለማ ሆነብህ፥ የጎርፍ ውሃም አሰጠመህ።
12እግዚአብሔር በሰማያት ከፍታ ላይ አይልምን? የዋክብትን ከፍታ ተመልከት ምን ያህል ከፍ ይላሉ!
13አንተም፦ 'እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?
14እንዳያየን ጥቅጥቅ ደመና ጋርዶታል፤ በሰማይም ክበብ ላይ ይራመዳል' አልህ።
15እነዚያ ኃጢአተኞች የሄዱበትን፥ የቀድሞውን መንገድ አንተ ደግሞ ትደግመዋለህን?
16ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም እንደ ወንዝ ፈሳሽ ተወሰደ።
17እግዚአብሔርንም፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።
18ነገር ግን እርሱ ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፤ የኃጥአን ምክር ከእኔ ይራቅ።
19ጻድቃን የነዚህን ፍጻሜ ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፤ ንጹሐንም በንቀት እዲህ በማለት ይስቁባቸዋል።
20'በእርግጥ በእኛ ላይ የተነሱ ጠፍተዋል፥ ሃብታቸውንም እሳት በልቶታል።'
21አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም መንገድ መልካም ነገር ያገኝሃል።
22እለምንሃለሁ፥ ከእርሱ አፉ መመሪያ ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤
23ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ እንደገና ትሰራለህ፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ አርቀህ ብትጥል፥
24የከበረ ሃብትህን በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
25ሁሉን የሚችል አምላክ የከበረ ሃብትና የተመረጠ ብር ይሆንልሃል።
26በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
27ወደ እርሱ ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፤ ስእለትህንም ለእርሱ ትሰጣለህ።
28በማናቸውም ነገር አዋጅ ትናገራለህ፥ እርሱም ይጸናልሃል፤ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።
29እግዚአብሔር ትዕቢተኛን ሰው ያዋርዳል፤ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።
30ንጹሕ ያልሆነውን ሰው እንኳ፤ በእጅህ ንጽሕና በኩል ይታደገዋል።