መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ቀጥሎም ኢዮብ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2ንግግሬን በጥንቃቄ ስሙ፤ የምታጽናኑኝም እንደዚህ ይሁን።
3እንድናገር ፍቀዱልኝ፤ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
4ቅሬታዬን የማሰማው ሰው ላይ ነውን? ትዕግስት ባጣስ፤ አይገባኝምን?
5እስቲ ተመልከቱኝና ተደነቁ፤ አፋችሁንም በእጃችሁ ያዙ።
6እኔ ስቃዬን ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፥ በፍርሃትምሥጋዬ ይንቀጠቀጣል።
7ለምን ኃጢአተኞች በሕይወት እስከ እርጅና ይኖራሉ? ለምን በሃይልስ ይበረታሉ?
8ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ተደላድለዋል፥ ልጆቻቸውም በአይናቸው ፊት ጸንተው ይኖራሉ።
9ቤቶቻቸው ያለስጋት ናቸው፥ የእግዚአብሔርም በትር በላያቸው የለም።
10ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩም በከንቱ አይወድቅም፤ ላማቸውም አትጨነግፍም በጊዜዋ ትወልዳለች፥ ።
11ሕፃናቶቻቸውን እንደ መንጋ ያሰማራሉ፥ ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ።
12በከበሮና በክራር ይዘምራሉ፥ በእምቢልታም ሙዚቃ ይደሰታሉ።
13ዕድሜያቸውንም በብልጥግና ይፈጽማሉ፤ በጸጥታም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።
14እግዚአብሔርንም፦" ከእኛ ራቅ፤ የመንገድህን እውቀት አንፈልግም' ይሉታል።
15እናመልከው ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ በመጸለይስ ምን ጥቅም ይገኛል? ይላሉ።
16እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? ከኃጥአን ምክር ጋር ምንም አይነት ህብረት የለኝም። የኃጥአን መብራት የጠፋው፥
17መቅሠፍትም በላያቸው የመጣባቸው ስንት ጊዜ ነው ፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው መቼ ነው፥
18በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ትቢያ የሆኑ ስንት ጊዜ ነው?
19እናንተ፦ 'እግዚአብሔር የበደለኛውን ቅጣት ለልጆቹ ይጠብቃል' ብላችኋል። ጥፋቱን እንዲያው ቅጣቱን ራሱ ይክፈል።
20የገዛ ዓይኖቹ ጥፋቱን ይዩ፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ቍጣ ራሱ ይጠጣ።
21ወራቶቹስ ካለቁ በኋላ፥ ከራሱ ሌላ ስለቤተሰቦቹ ምን ገዶት?
22በከፍታ ያሉትን ለሚፈርድ ለእግዚአብሔር ማን እውቀትን ሊያስተምረው ይችላል?
23አንድ ሰው በፍጹም ሰላምና ጤና ሲቀመጥ በሙሉ ብርታቱ ሳለ ይሞታል።
24በሰውነቱ ወተት ሞልቶአል፥ የአጥንቶቹም መቅን እርጥብና በጤንነት ናቸው።
25ሌላው ሰው ደግሞ መልካምን ነገር ፈጽሞ ሳይቀምስ፤ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።
26በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይጋደማሉ፥ ሁለቱንም ትል ይጨርሳቸዋል።
27አሳባችሁን፥ያሴራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።
28እናንተ፦ 'የልኡሉ ቤት የት አለ? ኃጢአተኛውም ሰው ይኖርበት የነበረ ድንኳን የት ነው?" ብላችኋል።
29መንገድ ተጓዦችን አልጠየቃችሁምን? ሊናገሩ የሚችሉትን ማስረጃ አታውቁምን?
30ኃጢአተኛው ከመቅሠፍት ቀን እንደ ተጠበቀ፥ ከቍጣው ቀን ዘወር እንደተደረገ።
31የሃጥያተኛውን መንገድ ፊት ለፊትl የሚቃወም ማን ነው? በሠራው ስራ የሚቀጣው ማን ነው?
32እርሱን ግን ወደ መቃብር ይሸከሙታል፥ ሰዎቹም መቃብሩን ይጠብቃሉ።
33የተቀበረበት አፈር እንኳ ይጣፍጥለታል፤ ሰዎች ሁሉ ይከተሉታል፥ እጅግ ብዙ ሕዝብም ከፊቱ ይሄዳል።
34መልሳችሁ ከውሸት በቀር ምንም ስለሌለበት፤ በከንቱ ነገር እንዴት ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ?
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።