መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ናዕማታዊውም ሶፋር ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2ከውስጤ ጭንቀት የተነሳ አሳቤ መልስ እንድሰጥ አስቸኮለኝ።
3የሚያሳፍረኝን ተግሣጽ ከአንተ ሰምቻለሁ፥ ነገር ግን ከመረዳቴ የሚያልፍ መንፈስ ይመልስልኛል።
4እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ካኖረበት፥ ከጥንት ጀምሮ እንዴት እንደ ነበር አታውቅም?
5የኃጢአተኛ መፈንጨት አጭር ፣ የአመጸኛም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?
6ቁመቱ እስከ ሰማይ ቢደርስ፥ ራሱም እስከ ደመና ቢሆን፥
7እንዲህ ያለ ሰው እንደ ምናምን ፈጽሞይጠፋል፤ አይተውት የነበሩም፦ ወዴት ነው? ይላሉ።
8እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤ በርግጥ እንደ ሌሊት ራእይ በርሮ ይጠፋል።
9ያየውም ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤ የነበረበት ስፍራም እንደገና አይመለከተውም።
10ልጆቹ ድሆችን ይቅርታ ይላሉ፤ እጆቹም ሀብቱን መመለስ ይገባቸዋል።
11አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት ተሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በአፈር ውስጥ ይተኛል።
12ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢደብቀው፥
13ምንም እንኳ እዚያው ቢያቆየው ባይለቅቀውም፥ በአፉ ውስጥ ቢይዘው፥
14ምግቡ በአንጀቱ ውስጥ ወደ መራራነት ይለወጣል፤ በውስጡ እንደ እባብ መርዝ ይሆንበታል።
15የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋል፤ እግዚአብሔርም ከሆዱ ያስወጣዋል።
16የእባብን መርዝ ይመጣል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።
17በማርና በቅቤ ፈሳሾች፥ በወንዞችም ተደስቶ አይኖርም።
18የደከመበትንም ሳይበላው መልሶ ይሰጣል፤ ባገኝውም ሃብት ደስ አይለውም።
19ድሆችን አስጨንቆአልና፥ ትቷቸዋልም፤ ያልሠራውንም ቤት በጉልበት ነጥቋል።
20በራሱ እርካታን ስለማያውቅ፤ የሚደሰትበትን አንድ ነገር ሊያስቀምጥ አይችልም።
21ሳያጠፋ የሚያስቀረው ነገር ስለማይኖር የሚዘልቅ ብልጽግና አይኖረውም።
22በሃብት ጠግቦ እያለ ይቸገራል፤ በድህነት ያሉ እጆች ሁሉ ይነሱበታል።
23ሆዱን ሊሞላ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር ብርቱ ቍጣውን ይሰድበታል፥ እየበላም ሳለ ያዘንብበታል።
24ከብረት መሣርያ ይሸሻል፥ የናስ ቀስት ግን ይወጋዋል።
25በርግጥ ቀስቱም ከኋላ ይወጋዋል፤ የጫፉም ብልጭታ በጉበቱ በኩል ይወጣል፤ ፍርሃትም ይመጣበታል።
26ለከበረ ዕቃው ፍጹም ጥፋት ተዘጋጅቶለታል፤ ያልተራገበ እሳት ይበላዋል፤ በድንኳኑም የተረፈውን ይጨርሰዋል።
27ሰማያት ኃጢአቱን ይገልጡበታል፥ ምድርም ምስክር ሆና ትነሣበታለች።
28የቤቱም ባለጠግነት ይጠፋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን የቤቱን ዕቃ ጎርፍ ይወስድበታል።
29ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።