1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2በቃላቶቻችሁ የምታሰቃዩኝና፥ የምትሰባብሩኝ እስከ መቼ ነው?
3አሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ በጭካኔ ስትበድሉኝም አላፈራችሁም።
4በርግጥ ተሳስቼ ቢሆን እንኳ፥ ስሕተቱ የእኔ ጉዳይ ይሆናል።
5በእርግጥ ራሳችሁን በላዬ ከፍ ብታደርጉ፥ እኔንም እንደተላላፊ ለሁሉ ብታስቆጥሩኝም፥
6ግን ደግሞ እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፥ በመረቡም እንደ ያዘኝ ማወቅ ነበረባችሁ።
7ስለ መበደሌ ልናገር ብጮኽም አልሰማም፤ እርዳታ ለማግኝት ብጠራም ፍትህ የለም።
8እንዳላልፍ መንገዴን አጥሮታል፥ በመንገዴም ላይ ጨለማ አኑሮበታል።
9ክብሬን ከላዬ ገፈፈ፥ ዘውዴንም ከራሴ ላይ አነሳ።
10እስክጠፋ ድረስ፥ በየአቅጣጫው ሰበረኝ፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፤
11ቍጣውንም በላዬ አነደደው፥ ከጠላቶቹም እንደ አንዱ አድርጎ ቈጠረኝ።
12ሠራዊቱ በአንድነት መጡብኝ፥ መወጣጫም በእኔ ላይ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
13ወንድሞቼን ከእኔ አራቃቸው፥ የሚያውቁኝም ፈጽመው ተለዩኝ።
14ዘመዶቼ ተዉኝ፥ የቅርብ ጓደኞቼም ረሱኝ።
15አንድ ወቅት በቤቴ በእንግድነት የተቀመጡ፥ ሴቶች ሰራተኞቼም እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ በፊታቸውም እንደ ባዕድ ሆንሁ።
16አገልጋዬን ተጣራሁ፥ በአፌም ለመንሁት ነገር ግን መልስ አልሰጠኝም።
17ትንፋሼም ለሚስቴ የሚያስጠላት ሆነ፥ ልመናዬም በገዛ ወንድሞቼና እህቶቼ ተጠላ።
18ሕፃናቶች እንኳ አንቋሸሹኝ፤ ለመናገር ብነሣም መልሰው ይናገሩኛል።
19የሚያማክሩኝ ጓደኞቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸው በእኔ ላይ ተነሱ።
20አጥንቴ ከሥጋዬና ከቆዳዬ ጋር ተጣበቀ በድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
21ጓደኞቼ ሆይ፥ እዘኑልኝ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና እዘኑልኝ።
22እግዚአብሔር እንደሆናችሁ ያክል ለምን ታሳድዱኛላችሁ? ሥጋዬን ማጥፋታችሁ ስለ ምን አይበቃችሁም?
23ኦ ምነው ቃሎቼ ቢጻፍ! ምነው በመጽሐፍ ቢታተሙ!
24ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ ተጽፎ፥ በዓለት ላይ ለዘላለም ቢቀረጽ!
25እኔ ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም በምድር ላይ እንዲቆም አውቃለሁ፥
26ይህ ቆዳዬ ማለትም ሰውነቴ ከጠፋ በኋላ፥ በአካሌ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
27አየዋለሁ፥ እኔ ራሴ በአጠገቤ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼ ይመለከቱታል፥ እንግዳም አይሆንብኝም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።
28“ 'እንዴት እናሳድደዋለን! የችግሩ ሥር በእርሱ ውስጥ ነው' ብትሉ፥
29ቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያስከትላልና፣ ሰይፍን ፍሩ፤ ፍርድ እንዳለም ታውቃላችሁ።”